አሜሪካ እና ሩሲያ የዩክሬን ግጭት ለመፍታት በድብቅ አዲስ እቅድ እያወጡ መሆናቸው ተዘገበ
19:26 19.11.2025 (የተሻሻለ: 19:34 19.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ እና ሩሲያ የዩክሬን ግጭት ለመፍታት በድብቅ አዲስ እቅድ እያወጡ መሆናቸው ተዘገበ
የታቀደው ባለ 28 ነጥብ የአሜሪካ እቅድ በአራት ዋና ዋና ጭብጦች የተዋቀረ ነው። የዩክሬን ሰላም፣ የደህንነት ዋስትናዎች፣ የአውሮፓ ደኅንነት እና አሜሪካ ከሩሲያ እና ከዩክሬን ጋር ወደፊት በሚኖራት ግንኙነት ዙሪያ ሆነው መለየታቸውን የአሜሪካ ሚዲያ ዘግቧል።
እቅዱ ከትራምፕ “ስኬታማ” የጋዛ ስምምነት ጥረቶች ተነሳሽነት እንዳመጣም ተገልጿል።
እቅዱ አወዛጋቢ አካባቢዎችን እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጣቸው ዝርዝር መረጃው ግልፅ አይደለም ሲል ዘገባው አክሏል።
የሩሲያ ከፍተኛ ባለሥልጣን በእቅዱ ላይ ያላቸውን ተስፋ የገለፁ ሲሆን የኪዬቭ እና የአውሮፓ አጋሮቿ ምላሽ እስካሁን አለመታወቁን ዘገባው አመልክቷል።
እቅዱን የመሩት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪቭ ጋር በሰፊው ተወያይተዋል ነው የተባለው።
ባለፈው ጥቅምት 14፣ ዲሚትሪቭ ከዋሽንግተን ባለሥልጣናት ጋር ስለወደፊቱ የአሜሪካ እና ሩሲያ ግንኙነት ለመወያየት አሜሪካ መጓዛቸው ይታወሳል። ሰኞ ዕለት ከአሜሪካ ሚዲያ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ-ምልልስ የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለሥልጣናት እስረኞችን መለዋወጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲነጋገሩ ቆይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X