የግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ፕሮጀክት ቅርፅ ይዟል - ፑቲን እና ኤል-ሲሲ የሰጧቸው ቁልፍ ንግግሮች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ፕሮጀክት ቅርፅ ይዟል - ፑቲን እና ኤል-ሲሲ የሰጧቸው ቁልፍ ንግግሮች
የግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ፕሮጀክት ቅርፅ ይዟል - ፑቲን እና ኤል-ሲሲ የሰጧቸው ቁልፍ ንግግሮች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.11.2025
ሰብስክራይብ

የግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ፕሮጀክት ቅርፅ ይዟል - ፑቲን እና ኤል-ሲሲ የሰጧቸው ቁልፍ ንግግሮች

ፑቲንና ኤል-ሲሲ በግብፅ ኤል-ዳባ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የመጀመሪያ ሪአክተር (ማብለያ) መትከል ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተሳተፉት ቭላዲሚር ፑቲን ዋና ዋና ሐሳቦች፦

🟠 በሩሲያ ተሳትፎ የሚካሄደው የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ ግንባታ "በተሳካ ሁኔታ እያደገ ነው"።

🟠 በቅርቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል።

🟠 የኃይል ማመንጫውን ሥራ ማስጀመር የግብፅን የኃይል ዋስትና በከፍተኛ ሁኔታ ያጠናክራል።

🟠 ሩሲያ በኒውክሌር ፕሮጀክቱ በእያንዳንዱ የትግበራ ደረጃ ግብፅን ትረዳለች።

🟠 በሞስኮና በካይሮ መካከል ያለው ግንኙነት በእኩልነት፣ በአክብሮትና የጋራ ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት ላይ የተመሠረተ ነው።

🟠 ፑቲን ለፕሬዝዳንት ሲሲ መልካም ልደት በመመኘት፣ ግብፅ "በሁሉም ፕሮጀክቶቿ ውስጥ የአቶሚክ ኃይል እንዲኖራት" ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የሰጡት ቁልፍ መግለጫዎች፦

የኒውክሌር ኃይል በግብፅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሲሆን፣ ኤል-ዳባ ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫ ነው።

የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው ለግብፅ የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት ዋስትናን ይሰጣታል።

ፕሮጀክቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን እየፈጠረ ነው።

ሥነ-ስርዓቱ "አስፈላጊ ምዕራፍ እንዲሁም ከሩሲያ ጋር ያለው የሁለትዮሽ ትብብር ውጤት" ነው።

ከሩሲያ ጋር ያለው ትብብር ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም፤ ሁለቱንም አገራት የሚጠቅሙ ተግባራዊ ዘርፎችንና ፕሮጀክቶችን ያካተተ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0