ሙስና በዩክሬን - "የአውሮፓ መሪዎች ያልደነገጡት የሥርዓቱ አካል በመሆናቸው ነው" - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
16:15 19.11.2025 (የተሻሻለ: 16:24 19.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሙስና በዩክሬን - "የአውሮፓ መሪዎች ያልደነገጡት የሥርዓቱ አካል በመሆናቸው ነው" - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ማሪያ ዛካሮቫ የአውሮፓ ፖለቲከኞች በዩክሬን ያለውን የሙስና መጠን ሳይገነዘቡ ቀርተው ሳይሆን እንዲያውም በቀጥታ ተሳታፊዎች ናቸው ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ዛካሮቫ በጥያቄ መልክ ሲያስቀምጡት፣ "ኡርሱላ ቮን ደር ላይን (የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት) ለአውሮፓ ሕብረት ክትባቶችን ምንም ዓይነት ቁጥጥር ሳይደረግበት በሞባይል የጽሑፍ መልእክት ከገዙ ምን ይመስላችኋል? በዩክሬን ያለውን ሁኔታ ወይም በኪዬቭ ያለውን አገዛዝ በተመለከተ አንዳች ዓይነት ቅዠት አላቸውን?"
"እነሱ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊዎች ነበሩ፤ ገንዘቡ ወዴት እንደሚሄድ ሳይገነዘበ ቀርተው አያውቁም። ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ ያውቁ ነበር... እና ይህ ገንዘብ ከእነሱ ጋር ግንኙነት ወዳላቸው አካውንቶች ገቢ ሆኗል" ሲሉ ዲፕሎማቷ አክለዋል፡፡
የቅርብ ጊዜው የሙስና ቅሌት በዩክሬን ይፋ የተደረገው ኅዳር 1 ሲሆን፣ የዩክሬን የፀረ-ሙስና ቢሮ በኢነርጂ ዘርፍ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከሕግ ውጭ ተመዝብሮ ከኋላው ያለውን "ወንጀለኛ ስርዓት" ለማጋለጥ 70 ምርመራዎችን ማካሄዱን ባወጀበት ወቅት ነው።
በጥርጣሬው ምክንያት አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዘለንስኪ የቅርብ አጋር የሆኑት ቲሙር ሚንዲች በምርመራው ከተጠረጠሩት መካከል ይገኙበታል። የኢነርጂና የፍትሕ ሚኒስትሮች ደግሞ ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X