- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ወደ ባህር የመመለስ ጥያቄ

የኢትዮጵያ ወደ ባህር የመመለስ ጥያቄ
ሰብስክራይብ

“የወደብ አጠቃቀም ሶስት አይነት ናቸው፡፡ አንደኛ አብሮ በማልማት፣ ሁለተኛ በሊዝ ኪራይ፣ ሶስተኛ ደግሞ ይዞታ በመለዋወጥ ነው፡፡ እና ይሄንን ማድረግ የምንችልበት መደራደር፣ መነጋገር፣ መወያየት እና መቀራረብ ነው፡፡ ስለዚህ ያነሳነው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እኛ ብቻ እንጠቀም አላልንም፡፡ እነሱም ይጠቀሙ ነው፡፡” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር መውጫ ለማግኘት ያቀረበቸውን ጥያቄ እና የምታደርገውን ጥረት በጥልቀት እንመረምራለን። በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ይህን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ደኅንነትና የክልላዊ ሁኔታ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ የሚያሳድረውን ጉዳይ እንዲሁም በዓለም አቶሚክ ሳምንት ስብሰባ የኢትዮጵያ ተሳትፎን ማዕከል አድርገን የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች አንቂ እና በአለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያ ተወካይ ከሆነው ከወጣት ኑርሁሴን አሊ ጋርም ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
አዳዲስ ዜናዎች
0