የሩሲያ የትምርት ቀን በሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
15:29 19.11.2025 (የተሻሻለ: 16:14 19.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የትምርት ቀን በሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
በዝግጅቱ ላይ ከ5 የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ አመራሮች እና ምሁራን፣ ከአዲስ አበባ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች የውጣጡ ተማሪዎች እና የትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ የአፍሪካ ሩሲያ ኔትዎርክ ዩኒቨርሲቲን ለመሠረቱት ሚካኤል ሉሞኖሶቭ መታሰቢያ የሚሆን የትምህርት ዐውደ-ርዕይም ቀርቧል።
ሥነ-ስርዓቱን በንግግር የከፈቱት በአዲስ አበባ የሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል ምክትል ኃላፊ ዲሚትሪ ብሪሎቭ እንዳሉት፣ አገራቸው ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እየሰጠች ያለውን ነጻ የትምህርት እድል በተለያዩ መስኮች እያስፋፋች ትገኛለች።
በዚህ ዓመትም በተለያዩ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች 155 ያህል ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ የማዕከሉ ምክትል ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል ሲል በስፍራው የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/4
© telegram sputnik_ethiopia

2/4
© telegram sputnik_ethiopia

3/4
© telegram sputnik_ethiopia

4/4
© telegram sputnik_ethiopia
1/4
© telegram sputnik_ethiopia
2/4
© telegram sputnik_ethiopia
3/4
© telegram sputnik_ethiopia
4/4
© telegram sputnik_ethiopia