የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ግዙፉ ኤ350 አንቀሳቃሽነት ቦታውን የሚያጠብቁለትን 6 ኤ350-900ኤስ ኤርባስ አውሮፕላኖችን አዘዘ
11:23 19.11.2025 (የተሻሻለ: 11:24 19.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ግዙፉ ኤ350 አንቀሳቃሽነት ቦታውን የሚያጠብቁለትን 6 ኤ350-900ኤስ ኤርባስ አውሮፕላኖችን አዘዘ
ስምምነቱን በዱባይ የአየር ትርዒት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና የኤርባስ የንግድ አውሮፕላኖች ቢዝነስ ሽያጭ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳንቴ ኤግዡፔሪ ተፈራርመዋል፡፡
“እንደ አኅጉሪቱ መሪ አየር መንገድ እና ትልቁ የኤ350 አንቀሳቃሽ እንደመሆናችን፣ ይህ ወሳኝ ትዕዛዝ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጉዞ ልምድ እየሰጠን እና በአፍሪካ የአቪዬሽን መሪነት ቦታችንን በማጠናከር በዘላቂነት የማደግ ርዕያችንን ይደግፋል።” ማለታቸውን አየር መንገዱ ድረ-ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል፡፡
ሳንቴ ኤግዡፔሪ በበኩላቸው፣ ከነባር የኤርባስ ደንበኛቸው እና በአፍሪካ የአቪዬሽን ልህቀት ምሳሌ ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከራቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀዋል፡፡
አዲሱ ትዕዛዝ አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን በቴክኖሎጂ ልህቀት፣ በነዳጅ ቆጣቢነት እና በአካባቢ ተስማሚነት ለማዘመን እና ለማስፋፋት ያለውን የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ የሚያጎላ መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X