ትራምፕ ሩሲያ እና ቻይና በአሜሪካ-መር የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛ ውሳኔ ላይ የያዙትን አቋም ዋጋ እንደሚሰጡት ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ትራምፕ ሩሲያ እና ቻይና በአሜሪካ-መር የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛ ውሳኔ ላይ የያዙትን አቋም ዋጋ እንደሚሰጡት ተናገሩ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ የሚደገፈውን የጋዛን የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምጽ በተሰጠ ጊዜ ሩሲያ እና ቻይና የወሰዱትን አቋም እንደሚያደንቁ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱም አገራት የተቃውሞ ድምጽ ከመስጠት ይልቅ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

"ስለዚህ እናደንቃለን፤ ምክንያቱም አንድ አሉታዊ ድምጽ ቢኖር ኖሮ አይሳካም ነበር፡፡ ስለዚህም ሰዎች መጽደቁን በተመለከቱ ጊዜ በጣም ደንግጠዋል" ሲሉ ትራምፕ አብራርተዋል፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት የአሜሪካን የጋዛን የተኩስ አቁም እና የዓለም አቀፍ ማረጋጊያ ኃይል እቅድን አጽድቋል። ሩሲያ እንደ ቻይና ሁሉ ተአቅቦን መወሳኗ ለፍልስጤም አስተዳደር እና በርካታ አረብ አገራት በጋዛ አዲስ ደም መፋሰስን ለማስወገድ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ብላለች።

የሩሲያ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዚያ የውሳኔ ሐሳቡ "የፍልስጤማውያን ሐሳቦች ምንም ግምት ውስጥ ሳይገቡ በሊግ ኦፍ ኔሽን የተሰጠውን የቅኝ ግዛት ልምምድ እና እንግሊዝ ለፍልስጤም የሰጠችውን ትእዛዝ የሚያስታውስ ነው" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0