https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ ይህ እድገት “በኦንላይን ወደ ፊት ልናሳካቸው ከምናስባቸው ኢ-ኮሜርስና ኢ-ገቨርንመንት እና ሌሎች ከዲጂታል ግንባታ ጋር... 18.11.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-11-18T19:15+0300
2025-11-18T19:15+0300
2025-11-18T19:24+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/2229954.jpg?1763483044
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ ይህ እድገት “በኦንላይን ወደ ፊት ልናሳካቸው ከምናስባቸው ኢ-ኮሜርስና ኢ-ገቨርንመንት እና ሌሎች ከዲጂታል ግንባታ ጋር የተያያዙ ተነሳሽነቶችን ለማሳካት ትልቅ መደላድል ይፈጥራል” ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉቀን ቀሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡የሚኒስቴሩ አመራሮች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በእቅድ የተያዙትንና አፈፃፀማቸውን ለምክር ቤቱ በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አገራዊ ተልዕኮችን ለማሳካት፦ የትራንዛክሽን አዋጅ፣ የግል ዳታ ጥበቃ፣ የዳታ ማዕከል ግንባታ፣ የክላውድ አገልግሎት መስጠት፣ የሞባይል ክፍያ ስርዓቶች፣ የዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም የተቋማት አቅም ግንባታ እንዲያድግ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብለዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታው፣ “የ2025 የዲጂታል ስትራቴጂ አጠናቀን 2030 ወደ ተግባር ለመግባት እየሠራን ነው፡፡ ... አገራችን በተለያዩ ዘርፎች ቴክኖሎጂን ተጠቅማ ልታመጣ ላሰበችው እምርታ ጥሩ መደላድልና ፍኖት እየተዘረጋ ነው፡፡” ማለታቸውን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2025
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
19:15 18.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 18.11.2025) የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
ይህ እድገት “በኦንላይን ወደ ፊት ልናሳካቸው ከምናስባቸው ኢ-ኮሜርስና ኢ-ገቨርንመንት እና ሌሎች ከዲጂታል ግንባታ ጋር የተያያዙ ተነሳሽነቶችን ለማሳካት ትልቅ መደላድል ይፈጥራል” ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉቀን ቀሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡
የሚኒስቴሩ አመራሮች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በእቅድ የተያዙትንና አፈፃፀማቸውን ለምክር ቤቱ በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አገራዊ ተልዕኮችን ለማሳካት፦
የትራንዛክሽን አዋጅ፣
የግል ዳታ ጥበቃ፣
የዳታ ማዕከል ግንባታ፣
የክላውድ አገልግሎት መስጠት፣
የሞባይል ክፍያ ስርዓቶች፣
የዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም
የተቋማት አቅም ግንባታ እንዲያድግ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው፣ “የ2025 የዲጂታል ስትራቴጂ አጠናቀን 2030 ወደ ተግባር ለመግባት እየሠራን ነው፡፡ ... አገራችን በተለያዩ ዘርፎች ቴክኖሎጂን ተጠቅማ ልታመጣ ላሰበችው እምርታ ጥሩ መደላድልና ፍኖት እየተዘረጋ ነው፡፡” ማለታቸውን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X