የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
19:19 18.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 18.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ 93 ሚሊዮን የሞባይል፣ 57.6 ሚሊዮን የበይነ-መረብ ተጠቃሚዎች የዲጂታል አገልግሎት መነቃቃት መፍጠራቸው ተገለፀ
ይህ እድገት “በኦንላይን ወደ ፊት ልናሳካቸው ከምናስባቸው ኢ-ኮሜርስና ኢ-ገቨርንመንት እና ሌሎች ከዲጂታል ግንባታ ጋር የተያያዙ ተነሳሽነቶችን ለማሳካት ትልቅ መደላድል ይፈጥራል” ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉቀን ቀሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡
የሚኒስቴሩ አመራሮች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በእቅድ የተያዙትንና አፈፃፀማቸውን ለምክር ቤቱ በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አገራዊ ተልዕኮችን ለማሳካት፦
የትራንዛክሽን አዋጅ፣
የግል ዳታ ጥበቃ፣
የዳታ ማዕከል ግንባታ፣
የክላውድ አገልግሎት መስጠት፣
የሞባይል ክፍያ ስርዓቶች፣
የዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም
የተቋማት አቅም ግንባታ እንዲያድግ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው፣ “የ2025 የዲጂታል ስትራቴጂ አጠናቀን 2030 ወደ ተግባር ለመግባት እየሠራን ነው፡፡ ... አገራችን በተለያዩ ዘርፎች ቴክኖሎጂን ተጠቅማ ልታመጣ ላሰበችው እምርታ ጥሩ መደላድልና ፍኖት እየተዘረጋ ነው፡፡” ማለታቸውን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X