የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
18:13 18.11.2025 (የተሻሻለ: 18:44 18.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቱክ ሴሪ አንዋር ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ወደ ምድረ-ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ መልካም ምኖታቸውን ገልፁላቸዋል፡፡
“ጉብኝትዎ በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው።” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር በቆይታቸው በሁለቱ አገራት 60ኛ ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ክብረ በዓል ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል። የብሪክስ አባል የሆነችው ኢትዮጵያ እና የብሪክስ አጋር የሆነችው ማሌዥያ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ ትብሎ ይጠበቃል፡፡
ዳቱክ ሴሪ አንዋር፣ ከዐቢይ አሕመድ በተጨማሪ መሪዎች ከኢንዱስትሪ መሪዎች እና ከኢስላማዊ ምሁራን ጋር እንደሚገናኙ ቀደም ሲል በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡
ልዑካቸውም የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ተንኩ ዳቱክ ሴሪ ዛፍሩል አብዱል አዚዝን፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የፌደራል ድንበሮች ሚኒስትር ዳቱክ ሴሪ ዛሊሃ ሙስታፋ ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ባለሥልጣናት እና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮችን ማካተቱ ተዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X






