ሩሲያ የ"አይተር" የሙቀት-ኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ወሳኝ መሣሪያዎችን አስረከበች

ሰብስክራይብ

ሩሲያ የ"አይተር" የሙቀት-ኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ወሳኝ መሣሪያዎችን አስረከበች

30 ቶን የሚመዝነው የመጀመሪያው የሩሲያ የሙከራ መሣሪያ በፈረንሳይ ፕሮጀክቱ ከሚገኝበት አካባቢ ደርሷል።

በደቡብ ፈረንሳይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት ኮከቦች ኃይል የሚያመነጩበትን ውህደት ሂደት በመድገም፣ በዚህ መንገድ የሚመነጨውን ኃይል በስፋት መጠቀምን ዓላማው ያደርጋል።

የ"አይተር" (ITER)* ፕሮጀክት ማዕከል ዳይሬክተር አናቶሊ ክራሲልኒኮቭ፣ “ይህ የሙከራ ቁስ በኃላፊነታችን ስር ከሚገኙት እጅግ ውስብስብ እና እውቀት የሚጠይቁ ሥርዓቶች ውስጥ አንዱ ነው” በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል።



በሮሳቶም የመረተው ይህ ልዩ ቁስ፣ የኃይል ማመንጫው ቁልፍ ክፍሎች የሆኑትን "ፖርት-ፕለግስ" (ተሰኪዎች) አሠራር ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ያገለግላል።

የአይተአር ፕሮጀክት ኃላፊ ሰርጂዮ ኦርላንዲ ይህንን “የሩሲያ ስኬት” እና ለፕሮግራሙ “ወሳኝ ፈጠራ” መሆኑን በመግለፅ አሞካሽተዋል።

ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ቢኖሩም፣ ሩሲያ 25 ዋና ዋና ሥርዓቶችን በማቅረብ በዚህ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክት ውስጥ ተሳትፎዋን እያጠናከረች እንዲሁም ቃሏን እያከበረች ነው።

* አይተር በውህደት ሂደት ኃይልን ለመፍጠር ያለመ ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ውህደት፣ ምርምር እና ምህንድስና ሜጋ ፕሮጀክት ነው።

ምስል በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0