የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ግጭት መከላከል፣ ሰላም ግንባታ እና ማኅበራዊ ትስስር ላይ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋገጠ
17:15 18.11.2025 (የተሻሻለ: 17:24 18.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ግጭት መከላከል፣ ሰላም ግንባታ እና ማኅበራዊ ትስስር ላይ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋገጠ
በሕብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴዎሌ፣ በዓለም አቀፍ እና በቀጣናዊ ተገዳሮቶች መካከል ሰላም ለማጠናከር የአፍሪካን ቅደመ-ግጭት እርምጃዎች በማጉላት፣ በባለድርሻ አካላት መካከል ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።
ኮሚሽነሩ ተግባራዊ የሰላም ግንባታ ስልቶችን ለማቅረብ የተዘጋጀውን የድህረ-ግጭት መልሶ ግንባታና ልማት ጆርናል ሁለተኛ እትም መጀመሩን ይፋ ማድረጋቸውን በስፍራው የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘገቧል።
"አፍሪካ ሕብረት ከግጭት በኋላ በማኅበረሰቡ ውስጥ የአእምሮ ጤና እና ሥነ-ልቦናዊ ድጋፍ አስፈላጊነትን በመገንዘብ፣ በመጪው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት በዚህ ርዕስ ላይ አዲስ ፖሊሲ ለመጀመር አቅዷል" ሲሉ አዲዎሌ ጠቁመዋል።
ኮሚሽነሩ የአፍሪካ ኅብረት በደቡብ ሱዳን፣ በቻድ ተፋሰስ፣ በታላላቅ ሐይቆች ክልል እና በሌሎች የግጭት ቀጠናዎች ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከተመድ የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት ጋር በቅርበት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የሚካሄዱ የሰላም ግንባታ ሂደቶች እንደ ሊቢያ፣ ሱዳን እና ምስራቅ ኮንጎ ባሉ የግጭት ቀጠናዎች ውስጥ የተጎዱ ህዝቦችን ሕይወት መለወጥን ማካተት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

