ኢትዮጵያ ሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሃ-ግብር በይፋ አስጀመረች
11:19 18.11.2025 (የተሻሻለ: 11:54 18.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሃ-ግብር በይፋ አስጀመረች
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ የመርሃ-ግብሩ መጀመር ኢትዮጵያ ግብርናዋን ለማዘመን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮቿን ሕይወት ለማሻሻል ለምታደርጋቸው ጥረቶች “ወሳኝ ምዕራፍ” መሆኑን በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡
ከ6 ዓመት በፊት ይፋ የሆነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሃ-ግብር፣ ለ4.4 ሚሊዮን አርሶ አደሮችን በመደገፍ፣ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የኩታ ገጠም የእርሻ ዘዴን እንዲተገብሩ በማድረግ በአገሪቱ ጠቅላላ የግብርና ምርት እድገት ላይ የ11 በመቶ ድርሻ አለው ተብሎ እንደሚገመትም ተናግረዋል።
አዲሱ አረጋ፣ በ9 ክልሎች በሚተገበረው የሁለተኛው ምዕራፍ 6.5 ሚሊዮን አርሶ አደሮችን ለመድረስና የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ጠንካራ ጥረት እንደሚደረግ መናገራቸውን በስፍራው የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


