ትራምፕ በቬንዙዌላ ላይ የምድር ዘመቻ ውሳኔን ማቆየታቸው ተዘገበ
10:46 18.11.2025 (የተሻሻለ: 10:54 18.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ በቬንዙዌላ ላይ የምድር ዘመቻ ውሳኔን ማቆየታቸው ተዘገበ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ቬንዙዌላ ላይ የመሬት ላይ ጥቃት ስለመሰንዘር እስካሁን ውሳኔ አላሳለፉም" ሲል ሲኤንኤን የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሷል።
ምንም እንኳን በቀጣናው ትልቅ የአሜሪካ ወታደራዊ ዝግጅት እና በርካታ የጥቃት አማራጮች ቢቀርቡላቸውም፣ ትራምፕ ጥቃቱ ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ጥንቁቅ ናቸው።
ጫና መፍጠር ብቻ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ከሥልጣን እንዲወርዱ እንደሚያስገድዳቻው ተስፋ እንዳላቸው ምንጮች ገልጸው፣ ዋሽንግተን በበኩሏ ለታደሰ ዲፕሎማሲ ማንኛውንም ክፍት አጋጣሚ ትጠብቃለች ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X