የናይጄሪያው አሠልጣኝ ለሽንፈታቸው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በ'መተት' ከሰሱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያው አሠልጣኝ ለሽንፈታቸው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በ'መተት' ከሰሱ
የናይጄሪያው አሠልጣኝ ለሽንፈታቸው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በ'መተት' ከሰሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.11.2025
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያው አሠልጣኝ ለሽንፈታቸው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በ'መተት' ከሰሱ

የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ተስፋቸው በፍፁም ቅጣት ምት ሽንፈት አብቅቷል፡፡

አሠልጣኝ ኤሪክ ቼሌ አንድ የኮንጐ ቡድን አባል አንዳች ነገር ሲበትን ቢመለከቱትም ጨዋታው በጦፈበት ጊዜ በመሆኑ ምንም አይነት ምልክት (ግብረ መልስ) አለመስጠታቸውን ተናግረዋል።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ናይጄሪያ በራባት ያደረጉት ጨዋታ ከጭማሪ ሠዓት በኋላ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ወደ መለያ ፍፁም ቅጣት ምት አምርተው ዲሞክራቲክ ኮንጎ 5 ለ 4 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

ድራማዊ የነበረው ጨዋታ በአራት የመለያ ምቶች እና በከባድ ዝናብ የታጀበ ነበር፡፡ የኮንጎው አንበል ቻንስል ምቤምባ ኮዳዎች ቢወረወሩበትም በተረጋጋ መንፈስ አሸናፊ ያደረጋቸውን ግብ አስቆጥሯል፤ ይህም አገሪቱ ከ24 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ እንድትሳተፍ አስችሏታል፡፡

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ቡድኑን ሽንፈቱን ወደ ኋላ ጥሎ፣ ከታህሳስ 12 እስከ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሞሮኮ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ፣ ዝግጅት ላይ እንዲያተኩሩ አሳስበዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0