የጋናዋ አክራ የፓን-አፍሪካን ተራማጅ ኃይሎች ዓለምአቀፍ ጉባኤ ልታስተናግድ ነው
16:10 17.11.2025 (የተሻሻለ: 16:14 17.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጋናዋ አክራ የፓን-አፍሪካን ተራማጅ ኃይሎች ዓለምአቀፍ ጉባኤ ልታስተናግድ ነው
አገሪቱ የታሪካዊውን ኮንግረስ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ጉባኤውን እንደምታስተናገድ ይፋ ተደርጓል።
በጉባኤው በአፍሪካ፣ በካሪቢያን እና በመላው ዓለም ከሚገኙ 57 አገራት እና ከዓለም አቀፍ የጥቁር ዲያስፖራ ድርጅቶች የተውጣጡ ከ200 በላይ ተወካዮች ራስን በራስ ለማስተዳደር እና ለክብር የጋራ ርዕይን ለመቅረጽ ይገናኛሉ።
"ከታሪካዊ ትውስታ ወደ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፍትሕ" በሚል መሪ ቃል የተሰየመው ይህ ዝግጅት ማክሰኞና ረቡዕ በክዋሜ ንክሩማ መታሰቢያ መቃብር (ሐውልት) ይካሄዳል።
ውይይቶቹ በአፍሪካ የአሁን እውነታዎች ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦
🟠 ካሳን የማግኘት ጥረት፣
🟠 ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እና
🟠 አዳዲስ የጥገኝነት ዓይነቶችን መዋጋት ይገኙበታል።
ዋና ዋናዎቹ ውጤቶች የሚከተሉት ይሆናሉ ፦
🟠 ለአፍሪካ ሉዓላዊነት እና ብልጽግና ስልታዊ ማዕቀፍ እንዲሁም
🟠 የተወካዮቹን የጋራ ዕይታ እና ቁርጠኝነት የሚይዘው የአክራ መግለጫ ማፅደቅ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X