ሲዲቢ አቪዬሽን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖችን 'በሊዝ' ውል ሰጠ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሲዲቢ አቪዬሽን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖችን 'በሊዝ' ውል ሰጠ
ሲዲቢ አቪዬሽን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖችን 'በሊዝ' ውል ሰጠ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.11.2025
ሰብስክራይብ

ሲዲቢ አቪዬሽን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖችን 'በሊዝ' ውል ሰጠ

በቻይና ልማት ባንክ ፋይናንሺያል ሊዝንግ ኮ. ሊሚትድ ሙሉ በሙሉ ባለቤትነት የተያዘው የአየርላንድ ቅርንጫፉ ሲዲቢ አቪዬሽን፣ ከግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይህንን "የሊዝ ውል" (ለረጅም ግዜ የሚቆይ የኪራይ ስምምነት) መፈራረሙን በትናንትናው ዕለት አስታውቋል።

የሲዲቢ አቪዬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጂ ቼን፣ “... የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአኅጉሪቱ (በአፍሪካ) ያለውን ትስስር ለማሳደግ ጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል፤ ይህም ጉዞን የበለጠ ተደራሽ ያደርገዋል። ብለዋል፡፡

ሁለቱ ማክስ አውሮፕላኖች በ2018 ዓ.ም ክረምት አካባቢ እንዲደርሱ መርሃ ግብር ተይዞላቸዋል።

ስምምነቱ አየር መንገዱ በጣም ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የሆኑ አውሮፕላኖች ለማሰባሰብ ያስቀመጠውን የዕድገት ስትራቴጂ የሚደገፍ መሆኑ ተዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0