ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የመንገድ ደህንነት ትራንስፎርሜሽን ጥረቶች ግንባር ቀደም ነች - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር
13:09 17.11.2025 (የተሻሻለ: 13:24 17.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የመንገድ ደህንነት ትራንስፎርሜሽን ጥረቶች ግንባር ቀደም ነች - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር
ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በአፍሪካ በየዓመቱ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀው፣ ኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን የኮሪደር ልማትን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋፋትና ለማዘመን፦
🟠 በመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ፣
🟠 በተሽከርካሪ ልማት፣
🟠 በኢንፎርመሽን ቴክኖሎጂ እና
🟠 በሰው ኃይል ልማት ከፍተኛና ጥረት እያደረገ መሆኑን ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የመሠረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ሜቴቦጌ በበኩላቸው ኢትዮጵያ "ለአፍሪካ አነቃቂ ምሳሌ" መሆኗን በመጥቀስ አሞካሽተዋታል ሲል የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቀን ሕዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ ተክብሯል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

