ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
11:33 17.11.2025 (የተሻሻለ: 11:44 17.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ “ሀገራቸን በዚህ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በንቁነት መሳተፏን በሚያረጋግጥ መንገድ ከፍታ ላይ ደርሷል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቋሙ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
“በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ትላልቅ የመረጃ ቋቶች፣ የመረጃ ፍለጋ፣ ሮቦቲክስ እና ኢመርሲቭ ቴክኖሎጂዎች አቅሙን በማጎልበት ላይ ይገኛል።”
በቅርቡ የተጀመረው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርት አፕ ማዕከል ደግሞ ይኽንን ከባቢ የበለጠ ያጠናክረዋልም ብለዋል፡፡
“ዜጎች ሐሳብ ብቻ ይዘው በመምጣት ፕሮቶታይፕ ለመፍጠር፣ ለማባዛት ብሎም ከግሉ ዘርፍ ኢንቬስተሮች ጋር እንዲገናኙ እድል ያመቻቻል። እስከ አሁን 200 ሐሳብ ፈጣሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመዋል።” በማለት አክለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሣሪያ ቤቱን ብሔራዊ አካባቢ ወደሚገኘው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንጻ አዛውሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


