🪖 በዩክሬን የሩሲያ ፍፁም ድል ለዓለም መረጋጋት ‘ጨዋታ ቀያሪ’ ይሆናል - የቀድሞ የአሜሪካ የደህንነት መኮንን
10:59 17.11.2025 (የተሻሻለ: 11:04 17.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
🪖 በዩክሬን የሩሲያ ፍፁም ድል ለዓለም መረጋጋት ‘ጨዋታ ቀያሪ’ ይሆናል - የቀድሞ የአሜሪካ የደህንነት መኮንን
"ይህ ድል አውሮፓ ዩክሬንን በመጠቀም ሩሲያ ላይ ትንኮሳ የመፈፀም አቅሟን ያመክናል። ለአሜሪካና እና ሩሲያ እውነተኛ ሰላም በር ይከፍታል፤ እናም መረጋጋትንም ያመጣል ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ በጣም አስፈላጊው ጉዳይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትቀዳጃው ሙሉ ድል ነው" ሲሉ ስኮት ሪተር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ሪተር “ሙሉ የሩሲያ ድል” ማለት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሩሲያ ያስቀመጧቸውን ግቦች በሙሉ ማሳካት ማለት መሆኑን አብራርተዋል።
ከዩክሬን ግጭት ባሻገር፣ ሪተር ብቅ ያሉ ኢኮኖሚዎች የሆኑት የብሪክስ ቡድን እድገት በመጪዎቹ ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት ውስጥ ሊታዩ ከሚገባቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል። የቡድኑ መብሰል ወይም መጠናከር አሁን ያለውን የዓለም ሥርዓት በእጅጉ ሊለውጥ እንደሚችል አስረድተዋል።
ተንታኙ ብሪክስ በምዕራቡ ዓለም ለሚመሩ ተቋማት ጥብቅ የሆነ ተቃራኒ ኃይል ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ከፍተኛ ችግሮች እንደሚገጥሙት አስጠንቅቀዋል።
ሪተር ሲያብራሩ፣ “ብሪክስ ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለው እንመለከታለን። በሌላ በኩል በእድገቱ ላይ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች እያሸነፈ፣ በሕንድ እና በቻይና መካከል ያለው ቀጠይነት ያለው አለመስማማት እንዳለ ሆኖ፣ አሜሪካ በቻይና እና በሩሲያ መካከል መጎራበጥ ለመፍጠር እንደምትሻ እያየን ነው" ብለዋል።
ሪተር ሌሎች የብሪክስ አገራትን ለይቶ ለማስቀረት አሜሪካ የምታደርገውን ጥረት አጉልተው አስረድተዋል። እንደ ምሳሌ ካዛክስታን ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት ለማድረግ የፈረመችው “የአብርሃም ስምምነቶች” በመጠቀም ዋሽንግተን በቡድኑ ላይ ያለውን ትኩረት ለማዞር እየሞከረች መሆኑን አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X