ቬንዙዌላ የአሜሪካ ወረራ የሚፈፀምባት "አዲሷ ቬትናም' ልትሆን ትችላለች
10:19 17.11.2025 (የተሻሻለ: 10:24 17.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቬንዙዌላ የአሜሪካ ወረራ የሚፈፀምባት "አዲሷ ቬትናም' ልትሆን ትችላለች
አሜሪካ ቬንዙዌላን ልትወር የምትችልበት ሁኔታ ቢኖርም፣ “እጅግ አጠራጣሪ” ነው፤ አሜሪካ ቬንዙዌላ ውስጥ መቆየት ይከብዳታል ሲሉ ብራዚላዊው ተንታኝ እና የቀድሞ የባሕር ኃይል መኮንን ሮቢንሰን ፋሪናዞ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ፋሪናዞ ይህ ሁኔታ ለአሜሪካ “አዲስ ቬትናም” ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፤ በዚህም እ.ኤ.አ. ከ1955 እስከ 1975 የተካሄደውን የቬትናም ጦርነት ጠቅሰዋል።
ተንታኙ አቋማቸውን ሲያብራሩ፣ ቬንዙዌላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝብ ያላት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሚሊሻና በጥሩ ሁኔታ የጦር መሣሪያ የታጠቀ መደበኛ ጦር ያላት ትልቅ አገር መሆኗን አስምረውበታል።
የአሜሪካ ጄራልድ አር. ፎርድ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች ጥምር ጦር በአሜሪካና በቬንዙዌላ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ቀደም ብሎ ካሪቢያን ባሕር ደርሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X