የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በሚቀጥሉት 14 ቀናት ከአማፂዎች ጋር በሰላም ስምምነት ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ መወያየት ይጀምራል ተባለ
20:02 16.11.2025 (የተሻሻለ: 20:04 16.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በሚቀጥሉት 14 ቀናት ከአማፂዎች ጋር በሰላም ስምምነት ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ መወያየት ይጀምራል ተባለ
የአፍሪካ ኅብረት ዛሬ ይፋ ባደረገው የሰላም ማዕቀፍ ስምምነት ጽሑፍ መሠረት፤ ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነቱ ሰሞኑን መግባባት የተደረሰባቸው ጉዳዮችን እና ስምንት ፕሮቶኮሎችን ያቀፈ ሲሆን ሁለቱ አስቀድመው ተፈርመዋል።
የሩዋንዳ እና የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኦሊቪየር ንዱሁንጊሬሄ እና ቴሬሴ ዋግነር የምስራቅ ኮንጎን ግጭት ለመፍታት ሰኔ 20 ቀን በዋሽንግተን የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል።
ተዋዋይ ወገኖች በኮንጎ ባለሥልጣናት እና በኤም23 አማፂያን መካከል እየተካሄደ ላለው የድርድር ሂደት ሙሉ ድጋፋቸውን መግለፃቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ሁለቱ ሀገራት የስምምነቱ አካል አድርገው በ2024 የፈረሙትን ግዴታ ለመከተል ቃል ገብተዋል፦
🟠 የሩዋንዳ ወታደሮች በ90 ቀናት ውስጥ እንዲወጡ፣
🟠 በ30 ቀናት ውስጥ የጋራ የደህንነት ትብብር አሠራር ማቋቋም፣
🟠 የኢኮኖሚ ውህደት ፕሮጀክቶችን ማስጀመር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X