በኢትዮጵያ የወባ ወረርሽኝ ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱ ተነገረ
16:49 16.11.2025 (የተሻሻለ: 16:54 16.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የወባ ወረርሽኝ ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱ ተነገረ
ባለፉት ሶስት ወራት በበሽታው ለተጠረጠሩ 5 ሚሊዮን 743 ሺህ በላይ ሰዎች በተደረገ ምርመራ 1 ሚሊዮን 979 ሺህ 597 ሰዎች ላይ ተህዋሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ገልፀዋል።
ከነዚህም ዉስጥ 113 ህይወታቸዉን በወባ ምክንያት አጥተዋል።
የበሽታው ስርጭት ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በግማሽ መቀነሱን ጠቁመዋል።
ሚኒስቴሩ የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ባለፉት ሦስት ወራት፦
ከስድስት ሚሊዮን በላይ አጎበር አከፋፍሏል።
ከሶስት ሚሊዮን በላይ ቤቶች ላይ የወባ መከላከያ ኬሚካል ርጭት አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X