የጢያ ትክል ድንጋይ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት እየለማ መሆኑ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጢያ ትክል ድንጋይ ከ3
የጢያ ትክል ድንጋይ ከ3 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.11.2025
ሰብስክራይብ

የጢያ ትክል ድንጋይ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት እየለማ መሆኑ ተገለፀ

መካነ ቅርሱ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ተደማሪ አቅም እንዲሆን በሚያስችል መልኩ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እየተሟሉለት ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

የ "ጢያ ፕሮጀክት" ሁለት ከተሞችን እንዲያገናኝ፣ የቱሪስት እና የተመራማሪዎችን ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ተደርጎ እየተሠራ ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደፈጠረ አገልግሎቱ ጨምሮ አመልክቷል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚገኘው ጢያ ትክል ድንጋይ በ1972 ዓ.ም ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ተብሎ በዩኔስኮ መመዝገቡ ይታወቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0