በጋዛ እስከ መጨረሻው ዋሻ ድረስ ትጥቅ እናስፈታለን - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ
13:24 16.11.2025 (የተሻሻለ: 13:34 16.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በጋዛ እስከ መጨረሻው ዋሻ ድረስ ትጥቅ እናስፈታለን - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ
የጋዛ ሰርጥን የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎች፦
የእስራኤል ጦር አውሮፕላኖች ዛሬ ጠዋት በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ ከተማ ካን ዩኒስ ምሥራቃዊ ሰፈሮች አምስት የአየር ጥቃቶችን እንደፈፀሙ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው አጠቃላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት መፍረሱን የጋዛ ማዘጋጃ ቤት የዕቅድ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል።
በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ከ13 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ባለፉት ቅርብ ቀናት ውስጥ በከባድ ዝናብ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩትም በከባድ የአየር ሁኔታ እና እየተባባሰ በመጣው የሰብዓዊ ሁኔታ ምክንያት የቀረውን ጥቂት ንብረታቸውን እንኳ አጥተዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት አድርጓል።
በካን ዩኒስ የሲቪል መከላከያ እንዳስታወቀው፤ እስካሁን የደረሰው እርዳታ ከሚያስፈልገው መጠን 15 በመቶ የተሻገረ አይደለም።
በጋዛ ሰርጥ የድንገተኛ ህክምና መውጫ መዘግየት ለ900 ሰዎች ሞት ምክንያት እንደሆነ እና አፋጣኝ ህክምና የሚያስፈልጋቸው 4ሺህ ህጻናትን ጨምሮ 16,500 ታካሚዎች አሁንም ለመጓዝ እየተጠባበቁ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X