የሱዳን ጦር በሰሜን ኮርዶፋን ሁለት አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩ ተነገረ
11:53 16.11.2025 (የተሻሻለ: 11:54 16.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን ጦር በሰሜን ኮርዶፋን ሁለት አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩ ተነገረ
▫ ከአማጺው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር ከተካሄደ ጠንካራ ውጊያ በኋላ ጦር ሠራዊቱ ኡም ዳም ሀጅ አህመድ እና ካዝጊልን በድጋሚ በመቆጣር በቡድኑ ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ማድረሱን ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ የሠራዊቱ አባላት ባለፈው ወር በአማጺዎቹ ተይዘው የነበሩትን ሁለቱን አካባቢዎች መቆጣጠራቸውን በማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፈው አረጋግጠዋል፡፡
እነዚህ ድሎች በሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በሚካሄደው ግጭት በቅርቡ በሱዳን ከሚገኙት ሦስቱ የኮርዶፋን ግዛቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መፈናቀላቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
▫ አማፂ ቡድኑ ከሰሜን ዳርፉር ሰሜናዊ ክፍሎች በስተቀር ከአምስቱ የዳርፉር ግዛቶች ሁሉንም በሚባል መልኩ የተቆጣጠረ ሲሆን የሱዳን ጦር በበኩሉ ካርቱምን ጨምሮ ቀሪዎቹን 13 የሱዳን ግዛቶች ይዟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X