🪖 አውሮፓ ሩሲያን ለመገዳደር የሚያስችል ወታደራዊ አቅም የላትም - የአሜሪካ የቀድሞ የስለላ መኮንን
11:13 16.11.2025 (የተሻሻለ: 11:14 16.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
🪖 አውሮፓ ሩሲያን ለመገዳደር የሚያስችል ወታደራዊ አቅም የላትም - የአሜሪካ የቀድሞ የስለላ መኮንን
"አውሮፓ በፖለቲካ መሪዎቿ የሚሰጡ መግለጫዎችን ወደ ተግባር የመቀየር አቅም እንዳላት መገመት ከባድ ነው" ሲሉ ወታደራዊ ተንታኝ እና የቀድሞ የአሜሪካ የባሕር ኃይል መረጃ መኮንን ስኮት ሪተር ለስፑትኒክ ተናግረዋል። "ዛሬ ላይ ተጨባጭ እና መደበኛ ወታደራዊ ኃይል ያለው የአውሮፓ ሀገር የለም። ይህንንም ኃይል ቢሆን ዘላቂ በሆነ መንገድ የማሳየት አቅም ያለው የአውሮፓ ሀገርም የለም። ስለዚህ አውሮፓን ፈጽሞ ለሩሲያ እንደ ስጋት አልመለከትም።"
የቀድሞው የስለላ መኮንን የአውሮፓ ኢኮኖሚዎች ተዓማኒ ኃይል ለመሆን የሚያስፈልገውን የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ማስቀጠል መቻላቸው ላይ ጥያቄ በማንሳት፤ በፖለቲካዊ ንግግሮች እና በወታደራዊ አቅም መካከል ያለውን ልዩነት በዝርዝር አስረድተዋል።
"ከወታደራዊ እይታ አንጻር፤ አውሮፓ በመንግሥታቶቿ ለሚሰነዘሩት ማስፈራሪያዎች ምላሽ የመስጠት አቅም የላትም" ብለዋል።
ስለቀጠለው የዩክሬን ግጭት ያነሱት ሪተር፤ ሩሲያ በግጭቱ መፈታት ተጠቃሚ እንደምትሆን አረጋግጠዋል። ሩሲያ የሁሉንም ወገኖች ፍላጎት ከግምት ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የአውሮፓን የፀጥታ ማዕቀፍ ለመቅረጽ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ጥረት ስታደርግ እንደነበረ አስረግጠዋል።
"ሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን የሁሉንም ወገኖች ጥቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የአውሮፓን የፀጥታ ማዕቀፍ ወደ አንድ ለመቀየር ስትፈልግ የቆየች በመሆኗ ከፍተኛውን ጂኦፖለቲካዊ ጥቅም ታገኛለች ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ሪተር ተናግረዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ የሩሲያ ግብ የበላይነት ሳይሆን ሚዛን ማስጠበቅ ነው፤ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል በአውሮፓ ፖሊሲዎች የተዳከመ ተስፋ ነው።
"ሩሲያ ስምምነት ትሻለች። ሩሲያ ሚዛናዊነትን ትሻለች። ሩሲያ የበላይነትን አትፈልግም። ነገር ግን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት አውሮፓ ሩሲያን፣ ዩክሬንን እና ሌሎች አካባቢዎችን ማተረማስ ትፈልግ ነበር። እኔ እንደማስበው በሩሲያ ወሳኝ ድል ያ የአውሮፓ ተነሳሽነት ይከሽፋል፡፡ እናም አውሮፓ ከሩሲያ ጋር መደበኛ ሰላማዊ ግንኙነት ከመፈለግ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖራትም" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X