የቶጎ መንግሥት ለ2026 በ14.4 በመቶ ከፍ ያለ 4.86 ቢሊዮን ዶላር በጀት አቀረበ
20:38 15.11.2025 (የተሻሻለ: 20:44 15.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቶጎ መንግሥት ለ2026 በ14.4 በመቶ ከፍ ያለ 4.86 ቢሊዮን ዶላር በጀት አቀረበ
የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የፋይናንስ ረቂቅ ሕጉን አጽድቋል።
በጀቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች፦
🟠 48 በመቶ ለማህበራዊ ዘርፍ፤ (ጤና፣ ትምህርት፣ ማህበራዊ ጥበቃ)፣
🟠 ለኢኮኖሚ ለውጥ ዘርፎች፤ (ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ዲጂታል)፣
🟠 ለግል ኢንቨስትመንት ማበረታቻ እና ለወጣቶችና ለሴቶች ዘላቂ የሥራ እድሎችን ለ
መፍጠር፣
🟠 ለፀጥታና የመከላከያ ዘርፍ መጠናከር።
በጀቱ በዋናነት የሚሸፈነው በመንግሥት ሀብቶች ሲሆን በ2025 ከተመደበው 6.2 በመቶ ጋር ሲነጻጸር በ2026 የ6.5 በመቶ እድገት ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በጀቱ በቀጣይ በብሔራዊ ምክር ቤት ቀጥሎም በሴኔት መታየት ይኖርበታል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X