አል-ቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ትጥቅ ካልፈታ ምንም ዓይነት ተኩስ አቁም ወይም የሰላም ስምምነት አይኖርም አሉ
13:28 15.11.2025 (የተሻሻለ: 13:34 15.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አል-ቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ትጥቅ ካልፈታ ምንም ዓይነት ተኩስ አቁም ወይም የሰላም ስምምነት አይኖርም አሉ
የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ጦርነቱ በሁሉም ሱዳናውያን ላይ ውድመት ቢያደርስም ብሔራዊ አንድነት ግን ፀንቶ ቀጥሏል ብለዋል።
ጄኔራሉ ዓመፀኞች እስከሚሸነፉ ድረስ ሠራዊቱ እንደሚዋጋ አስታውቀዋል፡፡ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎችን (አርኤስኤፍ) በግድያ፣ በማሰቃየት፣ በዝርፊያና በጭካኔ በመኮነን የድርድር ዕድሎችን ውድቅ አድርገዋል።
አል-ቡርሃን እንደነዚህ ያሉ "ገዳዮች እና ወንጀለኞች" ሱዳን ውስጥ ቦታ የላቸውም በማለት፤ ቅጥረኞች ተሰብስበው ትጥቃቸው እንዲፈታ ጠይቀዋል። አክለውም ግጭቱ በድርድር ሳይሆን ዓመፁን በማሸነፍ ብቻ እንደሚጠናቀቅ በመግለጽ ብቁ የሆኑ ዜጎች ሁሉ ውጊያውን እንዲቀላቀሉ አሳስበዋል።
የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማስዓድ ቡሎስ ተዋጊዎቹ ወገኖች የቀረበውን የሰብዓዊ እርዳታ ስምምነት እንዲቀበሉ ቀደም ሲል አሳስበዋል። አርኤስኤፍ ባለፈው ሳምንት በኳድ (አሜሪካ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ግብጽ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች) በቀረበዉ የእርቅ ሀሳብ መስማማቱን አስታውቆ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X