የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱዳን ኤል-ፋሸር በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ 'አስቸኳይ' ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱዳን ኤል-ፋሸር በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ 'አስቸኳይ' ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ
ውሳኔው የተላለፈው በፍጥነት እየተባባሰ የመጣውን ሁኔታ እና የሰብዓዊ ወንጀሎች እና የዘር ማጥፋት አደጋን ለማስቆም በተጠራው ልዩ ስብሰባ ነው።
የተመድ ውሳኔ የተጠርጣሪ ወንጀለኞችን "ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ"፤ የምርመራ ቡድኑ "ከተቻለ ማንነታቸውን እንዲለይ" ጥሪ አቅርቧል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ዋና ኃላፊ ቮልከር ተርክ በትናንትናው ዕለት የተካሄደውን ስብሰባ ሲከፍቱ "በኤል-ፋሸር የፈሰሰው የግፍ ደም ከህዋ በፎቶ ተነስቷል" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
በአካባቢው ያለው ግጭት በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል። ከ18 ወራት ከበባ በኋላ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘውን ስትራቴጂካዊ ከተማ ኤል-ፋሸርን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ስለሚፈጸሙ ግፎች የሚወጡ ሪፖርቶችም እየጨመሩ ነው።
በተመድ ግምት መሠረት፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከከተማዋ ተፈናቅለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ እና የተመድ ልዩ አማካሪ አዳማ ዲየንግ፤ "የዘር ማጥፋት አደጋው [...] እውነተኛ እና በየቀኑም እየጨመረ ነው" በማለት የሁኔታውን አስከፊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተመድ የሱዳን ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሃሰን ሃሚድ ሃሰን ይህንን ስጋት በማስተጋባት፤ ሀገሪቱ "በሕልውና ጦርነት" ውስጥ መሆኗን ተናግረዋል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ለአርኤስኤፍ ወታደራዊና ስልታዊ ድጋፍ እየሰጠች ነው ሲሉ ከሰዋል፤ ዩኤኢ ግን ይህንን ክስ አጥብቃ አስተባብላለች።
ℹ በሱዳን ጦር እና በአርኤስኤፍ መካከል ግጭቱ በሚያዝያ ወር 2015 ከጀመረ ወዲህ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ይህም በዓለም ላይ እጅግ የከፋ ከሆኑ የሰብዓዊ ቀውሶች አንዱን ፈጥሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X