ዚምባብዌ እና ዛምቢያ የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከፖለቲካዊ አጋርነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥምረት እየተሸጋገሩ ነው - ሚኒስትሮች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዚምባብዌ እና ዛምቢያ የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከፖለቲካዊ አጋርነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥምረት እየተሸጋገሩ ነው - ሚኒስትሮች
ዚምባብዌ እና ዛምቢያ የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከፖለቲካዊ አጋርነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥምረት እየተሸጋገሩ ነው - ሚኒስትሮች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.11.2025
ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ እና ዛምቢያ የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከፖለቲካዊ አጋርነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥምረት እየተሸጋገሩ ነው - ሚኒስትሮች

"ትብብራችንን ለዚምባብዌ እና ለዛምቢያ ሕዝቦች ተጨባጭ ጥቅሞች ወደ ማምጣት መቀየር ወሳኝ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ቀረጦች፣ ቀረጥ ነክ ያልሆኑ እና የቀረጥ መሰናክሎች ወደ ዜሮ መውረድ አለባቸው" ሲሉ የዙምባብዌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሞን ሙርዊራ በሀረሬ በተካሄደው የዚምባብዌ-ዛምቢያ የቢዝነስ ፎረም ላይ ተናግረዋል።

የዛምቢያ ንግድ ሚኒስትር ቺፖካ ሙሌንጋ ሁለቱም ሀገራት "ማሻሻያዎቹን ለመፈፀም የፖለቲካ ቁርጠኝነት" እንዳላቸው ገልፀዋል።

"ቀረጦች እና ቀረጥ ነክ ያልሆኑ ገደቦች የሁለትዮሽ ንግድን ለማስቆም ብቻ በቢሮክራቶች የተቀመጡ ሂደቶች ናቸው። በአውሮፓ እና በሌሎችም ቦታዎች ቀረጡን የፈጠሩ ሰዎችን እንመልከት፤ እነሱ ራሳቸው በመካከላቸው ቀረጥ የላቸውም" ሲሉ ሙሌንጋ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በተለይም በጋራ በሚተዳደረው የካሪባ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ ዙሪያ የኃይል ትብብርን በማጠናከር በሁለቱ ሀገራት እያደገ የመጣውን ፍላጎት ለማሟላት በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0