ህንድ ከ600 በላይ ኩባንያዎቿን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ልታሠማራ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱህንድ ከ600 በላይ ኩባንያዎቿን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ልታሠማራ ነው
ህንድ ከ600 በላይ ኩባንያዎቿን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ልታሠማራ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.11.2025
ሰብስክራይብ

ህንድ ከ600 በላይ ኩባንያዎቿን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይ ልታሠማራ ነው

ተቋማቱ በመንገድ፣ የቤቶቸ ልማት እና የኃይል መሠረት ልማት ላይ የፕሮጀክት ፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማበረታታት በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ተነሳሽነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

“የህንድ ተቋማትን በመንግሥት ከሚመሩ የመሠረት ልማት ፐሮክጀክቶች ጋር ለማጣመር ያለመው ውይይት እየተካሄደ ነው፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደረገ ምክክር የፋይናንስ ድጋፍ ማቅረብ የሚችሉ ኩባንያዎችን እየተለዩ ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራሂ ተናግረዋል፡፡

የህንድ እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በቀጣይ ህዳር ወር መጨረሻ በባንግሎር በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች አውደ ርዕይ ላይ ተጨማሪ የትብብር ዘርፎች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

አሁን ላይ ከ650 በላይ የህንድ ኩባንያዎች በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማማከር እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ በኢትዮጵያ ተሠማርተው እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0