ኢትዮጵያ 14ኛውን ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ በመጪው ህዳር 9 እና 10 ልታስተናግድ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 14ኛውን ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ በመጪው ህዳር 9 እና 10 ልታስተናግድ ነው
በጉባዔው ከ500 በላይ የሀገር ውስጥ ላኪዎች እና ከ16 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ ገዥዎች ይገኛሉ፡፡
የዘንድሮ ጉባዔ “የእሴት ሰንሰለቶቻችንን እያዳበርን ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቻችንን ማስፋት!” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡
🫘 በዘርፉ አዲስ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ 16 ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉም ተብሏል፡፡
🫛የኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ይህ ጉባኤ፤ የንግድ ግንኙነቶችን ለማጠናከርና አዳዲስ የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኤዳኦ አብዲ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ515 በላይ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች መኖራቸውን የማህበሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X