ኢትዮጵያ በ2022 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከ2.7 ቴራ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል እንደሚያስፈልጋት ጥናት አመላከተ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2022 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከ2
ኢትዮጵያ በ2022 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከ2 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2022 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከ2.7 ቴራ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል እንደሚያስፈልጋት ጥናት አመላከተ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ተፅዕኖ በተቋሙ የግሪድ ሲስተም ላይ በሚል ርዕስ ያስጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡

በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቁጥር ተከትሎ በ2017 ዓ.ም የነበረው 370 ጊጋ ዋት ሰዓት የኃይል ፍላጎት በ2022 ዓ.ም ወደ 2.7 ቴራ ዋት ሰዓት እንደሚያድግ በሰነዱ ተመላክቷል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ስትራቴጂክ እቅድን መረት በማድረግ የተከናወነው ጥናት፤ ከ2017-2022 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የኃይል አጠቃቀም የሚዳስስ መሆኑን የጥናቱ ቡድን መሪ ኢንጅነር ሀብታሙ አበበ ገልፀዋል፡፡

የኤሌክትሪክ አውቶብሶች በኃይል ፍጆታ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ ተብሏል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር በ2030 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ለማድረስ እንዳቀደ መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0