‘ተዓማኒ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሩሲያ-አፍሪካ 2025’ በሚል በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ተጠናቀቀ
18:45 14.11.2025 (የተሻሻለ: 22:24 14.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
‘ተዓማኒ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፤ ሩሲያ-አፍሪካ 2025’ በሚል በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ተጠናቀቀ
ጉባኤው ቁልፍ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ርዕሰ ጉዳዮችን ማለትም ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ፋይናንስ እና ስማርት ማኑፋክቸሪንግን ዳሷል፡፡
"ዩኒቨርሲቲያችን ከአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ስፔሻሊስቶችን ማሠልጠን ላይ ሁልግዜም ትኩረት ያደርግል፡፡ በዚህ ታሪካዊ አሻራ የማኖር ተግባር እንኮራለን፤ የትምህርት ትስስር ማጠናከራችንንም እንቀጥላለን" ሲሉ የሞስኮ የኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ኃላፊ ሰርጌ ኤሮክሂን፤ የሩሲያ-አፍሪካ የትምህርት ትብብር አስፈላጊነትን አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ የሳይንስ እና ባሕል ማዕከል ለ2026/2027 የትምህርት ዘመን በቀዳሚ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የስኮላርሺፕ ማመልከቻዎችን መቀበል ቀጥሏል።
ይህ እውቅ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያ ተማሪዎች በቀዳሚ የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማገዝ ያለመ ነው። የስኮላርሺፕ ዕድሉ ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነፃ ትምህርት፣ የዩኒቨርሲቲ ማረፊያ እና የዝግጅት ኮርስ ወጪን ይሸፍናል።
የነፃ ትምህርት ዕድሎቹ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የሚገኙ እና በሚከተሉት ብቻ የተገደቡ ባይሆኑም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ግን፦
ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ፣
ህክምና እና የጤና አገልግሎት፣
የተፈጥሮ ሳይንስ (ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ)፣
ኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ እና ኮምፒውተር ሳይንስ፣
ኢኮኖሚክስ እና ማኔጅመንት፣
የሰብዓዊነት ጥናት እና ዲፕሎማሲ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

