ከሩሲያ ጋር ያለን የንግድ ግንኙነት ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመግባት ትልቅ አቅም ነው - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር

ሰብስክራይብ

ከሩሲያ ጋር ያለን የንግድ ግንኙነት ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመግባት ትልቅ አቅም ነው - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የንግድ ትብብራቸውን የሚያጠናክሩ ስምምነቶችን እየፈጸሙ መሆናቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ይድነቃቸው ወርቁ ተናግረዋል።

"ሩሲያ በብዙ ነገሮች አያገዘችን ነው። እየተጠናከረ የመጣው የንግድ ግንኙነታችን የወጪ ንግዳችንን ከማሳደግ ባለፈ ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት ለመግባት ትልቅ መንደርደሪያ ሆኖ ያግዘናል" ሲሉ ስፑትኒክ አፍሪካ ላነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ የአኅጉሪቱን ነፃ የንግድ ቀጣና በመጠቀም በአፍሪካ ያላትን የገበያ መዳረሻ ለማስፋት እየሠራች መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0