ቡድን 20 በስሩ ለሚሳተፉ ሀገራት ያለውን አበርክቶ እና ጠቀሜታ ያስቀጥላል - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
16:11 14.11.2025 (የተሻሻለ: 16:14 14.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡድን 20 በስሩ ለሚሳተፉ ሀገራት ያለውን አበርክቶ እና ጠቀሜታ ያስቀጥላል - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
ሩሲያ በቡድን 20 ተግባራት ላይ ያላትን ፍላጎት ታስቀጥላለች ያሉት ዲሞትሪ ፔስኮቭ፤ ሞስኮ የጥምረቱን አጀንዳ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረግውን ጥረት ሁልግዜም ትቃወማለች ብለዋል፡፡
በፔስኮቭ የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
◾ ክሬምሊን በዓለም አቀፍ መድረኮች በመግባባት እጦት ምክንያት የመጨረሻ የጋራ ሰነዶች ላይ የማስተባብር ችግር እንዳለ ይገነዘባል።
◾ ሩሲያ አሜሪካ በካሪቢያን እና በቬንዙዌላ ዙሪያ አለመረጋጋት የሚፈጥሩ እርምጃዎችን እንደማትወስድ ተስፋ ታደርጋለች።
◾ ሩሲያ ሰሜን ኮሪያ ያደረገችውን በጎ እና ጀግነነት የተሞላበት እርዳታ ፈጽሞ አትረሳም።
◾ ፑቲን አርብ ዕለት ከፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር ይነጋገራሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X