ግዙፉ የሩሲያ የአልሙኒየም አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
14:44 14.11.2025 (የተሻሻለ: 14:54 14.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግዙፉ የሩሲያ የአልሙኒየም አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲኒግ እና የሩሲያው ሩሳል ኩባንያ 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዓመታዊ የአልሙኒየም ጥቅል የማምረት አቅም ያለውን ፋብሪካ ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ አቅራቢ እንድትሆን የሚያስችላት ነው ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ፦
በዘርፉ እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ማሟላት፣
የኢንዱስትሪ ልማትን ማገዝ፣
የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን መቀንስ፡፡
የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣ የተገለጸ ሲሆን ፋብሪካው ከሶስት እስከ አራት ዓመት ግዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተጠቅሷል፡፡
የ50 ዓመታት የአገልግሎት ዘመን የሚኖረው ፋብሪካ፤ 70 በመቶው በውጭ ብድር አቅርቦት እንደሚገነባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲኒግ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎ ፕሮጀክቱን ወደ ተግባር ለማስገባት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቲ መቋቋሙ ይፋ ተደርጓል፡፡
“የቦታ መረጣ እና አጠቃላይ የዳሰሳ ጥናትን የሚያካትቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከወዲሁ ተጀምረዋል” ሲል ተቋሙ አክሎ ገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

