🪖 የሩሲያ 5ኛ ትውልድ ሳርማት ስትራቴጂያዊ የሚሳኤል ሥርዓት - ክፍል አንድ

ሰብስክራይብ

🪖 የሩሲያ 5ኛ ትውልድ ሳርማት ስትራቴጂያዊ የሚሳኤል ሥርዓት - ክፍል አንድ

🟠 RS-28 ሳርማት በሚሳኤል ማከማቻ ታንከር ውስጥ(ሳይሎስ) ላይ ያለ አምስተኛ ትውልድ የሩሲያ ስትራቴጂያዊ ሚሳኤል ሥርዓት ነው። ከባድ የፈሳሽ ነዳጅ የሚሰራ አኅጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሉ (በኔቶ SS-X-30 ተብሎ ይጠራል)።

🟠 የአፈጣጠር እና የአገልግሎት ታሪክ

🟠 ቭላድሚር ፑቲን የሳርማትን ምርት ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳወቁት በ2011 ዓ.ም ነው። ፕሬዝዳንቱ ሳርማት ከ1970ዎቹ ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በአገልግሎት ላይ የነበረውን R-36M ቮይቮዳ ኮምፕሌክስ እንደሚተካ ገልጸዋል።

🟠 ሳርማት የሚለው ስም የተሰጠው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ4ኛው ክፍለ ዘመን እስከ ክርስቶስ ልደት በኋላ 6ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በአውሮፓ ከዲኔስተር ወንዝ እስከ ሰሜናዊ ካስፒያን ባህር ባለው የእርከን ዞን ይኖሩ የነበሩትን ኢራናዊ ተናጋሪ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚኖሩትን ህዝቦች በመጥቀስ ነው።

ሚሳኤሉ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ ነበር ። አዲሱ ሚሳኤል ሙሉ በሙሉ ሩሲያ-ሰራሽ በመሆኑ ልዩ ነበር፣ የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ከዚህ በፊት እንዲህ ያሉ ትላልቅ ወታደራዊ ምርቶችን ፈጥሮ አያውቅም።

የሚሳኤሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሞተር በ2009 ዓ.ም ተሞከረ፣ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል (ICBM) ሙከራም በታህሳስ 2010 ዓ.ም ተጀመረ።

የሚሳኤሉ የመጀመሪያ የበረራ ሙከራ የተካሄደው በሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ነበር። የማስጀመሪያው ዓላማዎች ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል። የልምምድ የጦር ጫፍ (ራሶች) በካምቻትካ በሚገኘው በኩራ የሙከራ ክልል ወደተጠቀሰው አካባቢ ደርሰዋል።

🟠 ፑቲን ውስብስቡን አስደናቂ ታክቲካዊ እና ቴክኒካዊ ባህሪያት ብቻ ሳይሆን፣ በአሰራሩ የአገር ውስጥ ቁሳቁሶችና እና የአካል ክፍሎች ብቻ ጥቅም ላይ መዋላቸውን፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች የመሳሪያውን ስብስብ (ኮምፕሌክስ) በተከታታይ ለማምረት እንደሚያቀልል ገልጸዋል።

በህዳር 14 ቀን 2015 የ አካዳሚሺያን ማኬቭ ስቴት ሮኬት ሴንተር አስተዳደር የሚሳኤሉ ተከታታይ ምርት መጀመሩን አስታውቋል። የክራስኖያርስክ ማሽን ግንባታ ፋብሪካ (የሮስኮስሞስ ስቴት አካል ኮርፖሬሽን) የሰርማትን ሚሳኤል መገጣጠምን በብቃት መከወን ችሎ ነበር።

በጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በ2018 ዓ.ም የሰርማት ሚሳኤል ያላቸው ስርዓቶች ለሙከራ የውጊያ አገልግሎት እንደሚውሉ እና በ2019 ዓ.ም ደግሞ ለውጊያ አገልግሎት እንደሚውሉ አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0