በአገሬ አሁንም ድረስ ይህ የብሪታንያ ሕዝቦች ቦታ ነው የሚባሉ ሥፍራዎች አሉ - የሴራሊዮን የመሬት ለሕይወት ኢኒሼቲቭ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ሰብስክራይብ

በአገሬ አሁንም ድረስ ይህ የብሪታንያ ሕዝቦች ቦታ ነው የሚባሉ ሥፍራዎች አሉ - የሴራሊዮን የመሬት ለሕይወት ኢኒሼቲቭ ዋና ሥራ  አስፈፃሚ

የቅኝ ግዛት የመሬት አስተዳደር መዋቅር በሴራሊዮን ላይ ዘመን ያልሻረው ከባድ ጠባሳ ማሳደሩን ጃኮብ ዊልሰን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ መዋቅሩ በመሬት ይዞታ ላይ የፈጠረው ኢ-ፍትሐዊነት የአገሬው ሕዝብ ጉስቁልና ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም አንስተዋል።

"የብሪታንያ ሰዎች መሬታችንን ወስደው የዘውድ ምድር ያሉትን አስተዳደር መሠረቱ። አሁንም ድረስ እዚህ አካባቢ ምንም ማድረግ አትችልም የምትባልባቸው ቦታዎች አሉ። ቅኝ ግዛት መሬት ከመግዛት እና ከመሸጥ ባለፈ ግብርናውንም ጎድቶታል።" ብለዋል።

ጃኮብ ዊልሰን ማኅበረሰቡ መሬቱን ለማስመለስ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መመለስ አንደሚገባም አጽዕኖት ሰጥተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0