ከሮሳቶም ጋር የተደረገው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ስምምነት በኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከሮሳቶም ጋር የተደረገው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ስምምነት በኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ
ከሮሳቶም ጋር የተደረገው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ስምምነት በኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.11.2025
ሰብስክራይብ

ከሮሳቶም ጋር የተደረገው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ስምምነት በኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ገለፁ

"ይህ በረዥም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነታችን ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት በጽኑ አምናለሁ" ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሞስኮ በተካሄደው የሩሲያ-ኢትዮጵያ የበይነ-መንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ሐሳቦች፦

🟠 የኢትዮጵያ በማዕድን ፍለጋ፣ የተፈጥሮ ሀብት ማውጣት እና በብረታ ብረት ሥራ ዘርፎች ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር ትብብር ትሻለች።

   "ሩሲያ በነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ማውጣት እንዲሁም ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በመላክ የዳበረ ልምድ አላት። የኢትዮጵያ ያልተነኩ ሰፊ ሀብቶች ለሩሲያ ኩባንያዎች ትልቅ ዕድሎችን ይሰጣሉ" ሲሉ ገልጸዋል።

🟠 በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ንግድ እያደገ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ 191.2 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፤ ኢትዮጵያ ለሩሲያ ገበያ በዋናነት ቡና እና አበባዎችን ትልካለች።

🟠 ሚኒስትሩ የንግድ መሰናክሎችን ማስወገድ፣ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ማሻሻል እና ቀጣይነት ያለው ትብብር ለማመቻቸት አማራጭ የፋይናንስ ዘዴዎችን መፈለግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

🟠 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በቅርቡ ወደ ሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት፣ የሁለትዮሽ አጋርነቱን እየጠነከረ ለመምጣቱ እንደ ማስረጃ አስታውሰዋል።

🟠 ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ላላት ታሪካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶች አድናቆት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተዋል፤ "በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ፣ ባህላዊ፣ ሳይንሳዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እያበበ ነው" ብለዋል።

🟠 ሀገራቱ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ትብብርን የሚያጠናክሩ በደርዘን የሚቆጠሩ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0