ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ሰገራን በመመርመር የሕጻናት ሳንባ ነቀርሳን የማወቅ አቅምን የሚጨምር አዲስ ግኝት ይፋ አደረጉ
16:32 12.11.2025 (የተሻሻለ: 16:34 12.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ሰገራን በመመርመር የሕጻናት ሳንባ ነቀርሳን የማወቅ አቅምን የሚጨምር አዲስ ግኝት ይፋ አደረጉ
ይህ ግኝት በበሽታው ምርመራ ላይ የነበረውን አስቸጋሪ እና ለአደጋ የተጋለጠ እርግጠኝነቱም ከ20 እስከ 50 በመቶ የነበረውን የአክታ ናሙና ምርመራ በተሻለ መልኩ የሚቀይር መሆኑ ተገልጿል።
በ557 ሕፃናት ላይ በተደረገው በዚህ ጥናት ከጥምር ማጣቀሻ መመዘኛዎችን ጋር ሲነፃፀር በሰገራ የሚሠራው ምርመራ በአክታ ከሚደረገው ምርመራ በበለጠ እስከ 85.5 በመቶ የደረሰ ከፍተኛ ትክክለኛነት አሳይቷል፡፡
የሰገራ ትንተና በሕጻናት ላይ የሳንባ ነቀርሳን ለመመርመር እጅግ በጣም ትክክለኛ እና ተግባራዊ ዘዴ መሆኑን በዓለም አቀፍ የሳይንስ ደረ-ገጽ ላይ የታተመው የምርመር ውጤት አስነብቧል።
ግኝቱ የአየር መተንፈሻ አካላት ናሙናዎች ለማግኘት አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ ተስፋ ሰጪ አማራጭ ሆኗል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X