ሩሲያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት እድገት ተመልክታለች፤ ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ ናት ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት እድገት ተመልክታለች፤ ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ ናት ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ሩሲያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት እድገት ተመልክታለች፤ ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ ናት ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.11.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት እድገት ተመልክታለች፤ ድጋፍ ለማድረግም ዝግጁ ናት ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ

"ኢትዮጵያ የዕድገቷን ፍጥነት ለማስጠበቅ፣ እየጨመረ የመጣውን የክህሎት የሀብት እና የቴክኖሎጂዎች ፍላጎት ማሟላት ይኖርባታል" ሲሉ የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ጠቆሙ።

በዛሬው ዕለት ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የበይነ-መንግሥታት ኮሚሽን 9ኛው ስብሰባ አካሂደዋል።

ሬሼትኒኮቭ ኢትዮጵያ በበለጸጉ ሀብቶቿ፣ እየጨመረ በመጣው የሕዝብ ቁጥሯ፣ በሰለጠነው የሰው ኃይልና እየተሻሻለ ባለው የሕግ ማዕቀፍ የምትመራ በዓለም ፈጣን ዕድገት ካላቸው ኢኮኖሚዎች አንዷ መሆኗን አስምረውበታል። ይህም ለዓለም አቀፍ አጋሮች ይበልጥ ዝግጁ እና ግልፅ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሩሲያ ቁልፍ የአፍሪካ አጋር በመሆን ወሳኝ ሚና አላት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው፤ በሀገራቱ መካከል የጋራ የንግድ ፍላጎት እየጨመረ እንዲሁም የጋራ ፕሮጀክቶች እየበዙ መሆናቸውንም አክለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0