ሩሲያ በሠራዊቷ ውስጥ አዲስ የድሮን ክፍለ ጦር ማቋቋሟን ምክትል አዛዡ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በሠራዊቷ ውስጥ አዲስ የድሮን ክፍለ ጦር ማቋቋሟን ምክትል አዛዡ ገለፁ
ሩሲያ በሠራዊቷ ውስጥ አዲስ የድሮን ክፍለ ጦር ማቋቋሟን ምክትል አዛዡ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.11.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በሠራዊቷ ውስጥ አዲስ የድሮን ክፍለ ጦር ማቋቋሟን ምክትል አዛዡ ገለፁ

ሰርጌይ ኢሽቱጋኖቭ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ አሁን ላይ ቋሚ የድሮን ክፍለ ጦሮችና አሃዶች በመላ ሀገሪቱ ተቋቁመዋል።

አዲሱ ቅርንጫፍ የታወቀ የአደረጃጀት መዋቅር፣ የተሰየመ አዛዥና በአገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋሙ ወታደራዊ አመራር አካላት አሉት ሲሉ ጠቁመዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ቤሎውሶቭ ይህ የሠራዊት ቅርንጫፍ እንዲቋቋም ሐሳብ ያቀረቡት በታህሳስ 2017 ዓ.ም ፑቲን ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ነበር።

ፑቲን የሰው አልባ አውሮፕላንኖች የሚሰሩበት (የበረራ) ርቀታቸውን፣ ራስን ማስተዳደራቸውን እና ጣልቃ ገብነትን የመቋቋም አቅማቸውን ማሳደግን ጨምሮ ታክቲካዊ እና ቴክኒካዊ ባህርያቸውን በማሻሻል ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

  ባለፈው ሰኔ ፕሬዝዳንት ፑቲን፣ የሩሲያ አዲስ የመንግሥት የጦር መሣሪያዎች መርሃ ግብር፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚጠቀሙ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ የላቁ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ማተኮር አለበት ብለው ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0