
የሩሲያ የኒውክሌር ሦስትዮሽ ወይም ሶስት የኒውክሌር ዓይነቶች (የመሬት ፣ የባህር እና ስትራቴጂክ ቦምቦች) በአዲስ የጦር መሳሪያዎች ተሞልቷል። ሞስኮ ለበዛው የጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎቿ የሰጠችው ምላሽ የሚከተሉት ናቸው፦
ቡሬቬስትኒክ፣ ያልተገደበ ርቀት ያለው የክሩዝ ሚሳኤል
ፖሰይዶን፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ያለው የውሃ ውስጥ ድሮን
ሳርማት፣ ከምድር ምህዋር በታች መብረር የሚችል ባሊስቲክ ሚሳኤል
ኦሬሽኒክ፣ መካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ ሚሳኤል ያለው የሩሲያ የቅርብ ጊዜ የሚሳኤል ስርዓት
የቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል እና የፖሰይዶን ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪ (ድሮውን) በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሙሉ ስትራቴጂካዊ እኩልነትን እንደሚያረጋግጡ ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል። ሩሲያ ማንንም አታስፈራራም ፣ ከሌሎች ሀገራት ም ጋር ለአዳዲስ የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነቶች ሁልጊዜ በሯ ክፍት ነው ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
ልዩ ባህሪያቸው በዓለም ላይ ብዙዎችን ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፣ በሚፈጽሙት አንድ ጥቃት የታሪክን ሂደት የመቀየር ችሎታቸው ‘የምጽዓት ቀን የጦር መሳሪያዎች’ የሚል አስፈሪ ቅጽል ስም አስገኝቶላቸዋል።
ቡሬቬስትኒክ (ስያሜ 9M730፤ የኔቶ ኮድ ስም SSC-X-9 ስካይፎል) የሩሲያ አህጉር አቋራጭ የኒውክሌርክሩዝ ሚሳኤል ነው። የአየር መከላከያ እና የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶችን ማለፍ የሚችል እና ተተኳሽ የኒውክሌር አረሮችን በረጅም ርቀት ለማድረስ የተነደፈ ነው።
ዋና ባህሪው የኑክሌር ሞተሩ ነው። የአቪዬሽን ኬሮሲን፣ ሲንቴቲክ ወይም ጠጣር ነዳጅ ከሚጠቀሙ እና የተወሰነ ክልል ካላቸው ከተለመዱ የክሩዝ ሚሳኤሎች በተለየ፤ የቡሬቬስትኒክ ሞተር በኒውክሌር ኃይል ይሠራል። ይህም ለሚሳኤሉ፡-
ከሞላጎደል ያልተገደበ የበረራ ክልል፣
ረጅምየበረራ ጊዜ፣
አቅጣጫውንየመቀየር እና ከማንኛውም አቅጣጫ የማጥቃት አቅምን ይሰጣል።
ረጅም የአየር ላይ ቆይታው እና 'ለረጅም ጊዜ የመቃኘት' አቅሙ ሚሳኤሉ ካልተጠበቁ አቅጣጫዎች ወደ ጠላት ግዛት እንዲገባ ያስችለዋል። ለአብነትም ክትትል አነስተኛ በሆነባቸው የዋልታ መስመሮች የአየር መከላከያ እና የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶችን ማለፍ ይችላል። ይህ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የማጨናገፊያ መመሪያ ስርዓቶችን ሥራ ያወሳስባል። ዝቅተኛ ከፍታ፣ ተለዋዋጭ አቅጣጫ እና ረጅም የበረራ ጊዜ ጥምረት ለክትትል ስርዓቶች 'ውዥንብር' ይፈጥራል።
"አጠቃቀማቸው በመከላከያ ኢንዱስትሪው ብቻ ሳይሆን በብዙ የሲቪል ዘርፎች ውስጥ በርካታ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ብሔራዊ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞችን በመተግበር ረገድ እመርታዎችን እንድናሳካ ያስችለናል። ከእነዚህም ውስጥ ለአነስተኛ የኒውክሌር ኃይል፣ በአርክቲክዞን የኃይል ማመንጫዎችን ለመፍጠር እና በአሁኑ ጊዜ እያለማን እና እየሠራንበት ለምንገኘው የከባድ መንኮራኩር እንዲሁም በጨረቃ ወደፊት ለምንገባው ጣቢያ የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ የጥልቅ እና ቅርብ የጠፈር አሰሳን ይካትታል" ሲሉ ፑቲንበህዳር ወር 2018 ዓ.ም ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፖፑላር ሜካኒክስ መጽሔት የሩሲያ ፖሳይደን መሳሪያን “አስፈሪ የምፅዓት ቀን ቶርፔዶ” ሲል ገልጾታል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የካቲት 22፣ 2010 ዓ.ም በሩሲያ ፓርላማ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሀገሪቱ “ ከሰርጓጅ መርከቦች፣ በጣም ዘመናዊ ከሆኑ ቶርፔዶዎችእና ፈጣኖቹን ሳይቀር ከሁሉም አይነት የባሕር ጦር መርከቦች፤ በከፍተኛ ጥልቀት እና አህጉራዊ ክልሎችን በፍጥነትማካለል የሚችሉ ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን” እንደሠራች አስታውቀዋል።
▪️ፖሴይዶኖች የዚህ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪ ተሸካሚ በሆኑ የተወሰኑ የኒውክሌርሰርጓጅ መርከቦች ብቻ ነው የሚሠሩት፡፡
▪️ በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም በሴቬሮድቪንስክ የሚገኘው ሴቭማሽ የመርከብአምራች ኩባንያ ፕሮጀክት949 የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ቤልጎሮድን ጀመረ። ይህ ለፖሳይደንተብሎ የተነደፈ የሙከራ ሰርጓጅ መርከብ ነው።
▪️ ጥቅምት 22፣ 2018 ዓ.ም ለፖሳይደንየሚመጥን ሆኖ የተሠራው የካባሮቭስክ የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ተመረቀ። መርከቡ ለፖሳይደን የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ኮምፕሌክስ በተለየ የተነደፈ እናየተገነባ ነው።
ዝቅተኛ የድምጽ መጠን
ከፍተኛ የመንቀሳቀስ ችሎታ
ከሞላ ጎደል ለጠላት ፈጽሞ የማይበገር
የተለመደ አይነት እና በኒውክሌር ጦር ራሶች ሊታጠቅ ይችላል
‘እነዚህን ሚሳኤሎች መትቶ የመጣል እድል የለም’ ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል።
• መካከለኛ ክልል - ከ1,000 እስከ 5,500 ኪሎ ሜትር።
• ፍጥነት- 10 ማች(12,380 ኪ.ሜ በሰዓት፣ በግምት 2.5-3 ኪ.ሜ በሰከንድ)።
• የጦር ጭንቅላት የሙቀት መጠን - 4,000 ሴልሺየስ።
• የጦር ጭንቅላት - በግምት 1.5 ቶን።
• እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ ሚሳኤሉ ጠንጣር ነዳጅ ያለው ሲሆን ሁለቱንም፤ መደበኛ እና የኒውክሌር ጦር ጭንቅላቶችን እንዲሁም እያንዳንዳቸው 150 ኪሎ ቶን የሚሆኑ ከ3 እስከ 6 የሙቀት ኒውክሌር ጦር ጭንቅላቶችን ሊሸከም ይችላል።
• በኒውክሌር ስሪቱ፣ በአጠቃላይ 900 ኪሎ ቶን (45 ሂሮሺማዎች) የጦር ጭንቅላቶችን ማድረስ ይችላል።
• ከ3-4 የተጠናከሩ ወለሎች ጥልቀት ላይ ኢላማዎችን መምታት ይችላል።
ኦሬሽኒክ ተመትቶ ሊወድቅ የሚችለው በመጀመሪያ የበረራ ምዕራፍ ላይ ብቻ ነው። የጦር ጭንቅላቶቹ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ኢላማው ይቀርባሉ። ኦሬሽኒክን በመጨረሻው ደረጃ ማጨናገፍ የማይቻል ነው።
ሚሳኤሉ በደንብ የተጠበቁ እና ጥልቅ ኢላማዎችን መምታት የሚችል ሲሆን የአስደንጋጭ ንጥረ ነገሮቹ የሙቀት መጠን 4,000 ዲግሪ ሴልሺየስ ይደርሳል፡፡ የዚህ ሚሳኤል ከፍተኛ ኣጠቃቀም 'ከኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ጋር ሊወዳደር ይችላል' ሲሉ ፑቲን ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ተናግረዋል። 'በፍንዳታው ማዕከል ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ወደ ቁርጥራጮች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ቅንጣቶች ተከፋፍሎ ወደ አቧራ ይለወጣል' ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሚሳኤሉ በሩሲያ ዘመናዊ እና ፈር ቀዳጅ ቴክኖሎጂዎች የተሠራ ሙሉ በሙሉ አዲስ ልማት መሆኑን ገልጸዋል። ሩሲያ ከወዲሁ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ የሚሳኤል ክምችቶች ያሏት ሲሆን በብዛት የማምረት ሂደቱም ተጀምሯል።
ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የሩሲያ ጦር ኃይሎች በዴኔፕሮፔትሮቭስክ (ዲኒፐር) በሚገኘው የዩክሬን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት በአንዱ ላይ በኦሬሽኒክ ኒውክሌር አልባ ሃይፐርሶኒክ መሳሪያ የተቀናጀ ጥቃት ፈጽመዋል። ምንጮች ኢላማው ከዩክሬን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምሌክስ አንዱ የሆነው የዩዝማሽ ፋብሪካ እንደነበር ጠቁመዋል። በሥፍራው የኪዬቭ አገዛዝ የራሱን የባለስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከረ ነበር። ሁሉም የሚሳኤሉ የጦር ጭንቅላቶች ኢላማቸውን መትተዋል።
የአጸፋ ጥቃት መብት፤ ሩሲያ የጦር መሣሪያዎቻቸውን በሩሲያ ኢላማዎች ላይ በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ ይሁንታቸውን በሚቸሩ አገራት ውስጥ ባሉ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የራሷን የጦር መሣሪያዎች የመጠቀም መብት እንዳላት ታምናለች።
አቻ ምላሽ፤ የጥቃትድርጊቶች ከተባባሱ ሩሲያ በእኩል ቁርጠኝነት እና አቻ (በአይነት) ምላሽ ትሰጣለች።
ለገዥ ሊሂቃን ማስጠንቀቂያ፤ ፑቲን ወታደራዊሠራዊቸውንበሩሲያ ላይ ለመጠቀም ለወጠኑ አገራት ገዥ ልሂቃን ስለ ዕቅዳቸው በቁም ነገር እንዲያስቡበት መክረዋል።
▫️ ጥቃቱ የተፈፀመው ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ላይ የጦር ስልታዊ ሚሳኤል ስርዓት (ATACMS) እና “ስቶርም ሻዶ” የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን ለመጠቀሟ ምላሽ ነው።
▫️ ኦሬሽኒክ የኔቶአገራት በሩሲያ ላይለሚወስዱት ጠበኛ እርምጃዎች ምላሽ በውጊያ ሁኔታዎች እየተሞከረ ነው።
▫️ ሩሲያ በኦሬሽኒክን ዩክሬንን ስትመታ፣ ሰላማዊ ሰዎች ከአደገኛ አካባቢዎችን አስቀድመው ለቅቀው እንዲወጡ ዕድል ትሰጣለች።
ሩሲያ ከኦሬሽኒክ ጋር የሚመሳሰሉ በሙከራ ሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ ስርዓቶችእንዳሏትም ጠቁመዋል፡፡ ''እኛ እንደምናውቀው፣ እናንተም እንደምታውቁት፣ በዓለም ላይ ማንም ሌላ አካል እስካሁን እንደዚህ አይነት መሳሪያ የለውም። አዎን፣ ይዋል ይደር እንጂ በሌሎች መሪ ሀገራት ውስጥ ይገኛሉ፤ እዚያ ምን ዓይነት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ እናውቃለን። ግን ይህ የሚሆነው ነገ [ወደፊት] ነው። በአንድ ዓመት፣ ወይም በሁለት ዓመት። እኛ ግን ይህ ሥርዓት ዛሬ አለን። እናም ይህ አስፈላጊ ነው፡፡'' ሲሉ የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አጽንኦት ሰጥተው።
▪️ በታኅሣሥ 2017 ዓ.ም ፣ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ፣ ኦሬሽኒክ ሥርዓት ጨምሮ የቅርብ ጊዜዎቹን የሩሲያ የጦር መሣሪያዎች በቤላሩስ ግዛት ውስጥ እንዲሰማሩ ቭላድሚር ፑቲንን ጠይቀዋል።
▪️ ነሐሴ 2 ቀን2017 ዓ.ም ሉካሼንኮ ለኦሬሽኒክ የመጀመሪያ ቦታዎች አስቀድመው መሰናዳታቸውን ይፋ አድርገዋል። በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም መሣሪያው በውጊያ ዝግጁነት ላይ ይቀመጣል።
▪️ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የመጀመሪያው ተከታታይ ኦሬሽኒክ ሥርዓት ለወታደሮቹ መድረሱን ከፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በቫላም (ካሬሊያ) ባደረጉት ስብሰባ ወቅት አስታውቀዋል።
▪️ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ሩሲያየኦሬሽኒክ ተከታታይ ምርት መጀመሯን ቭላድሚር ፑቲን ይፋ አድርገዋል።
ቭላድሚር ፑቲን የሳርማትን ምርት ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳወቁት በ2011 ዓ.ም ነው። ፕሬዚዳንቱ ሳርማት ከ1970ዎቹ ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በአገልግሎት ላይ የነበረውን R-36M ቮይቮዳ ኮምፕሌክስ እንደሚተካ ገልጸዋል።
ሳርማት የሚለው ስም የተሰጠው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ4ኛው ክፍለ ዘመን እስከ ክርስቶስ ልደት በኋላ 6ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በአውሮፓ ከዲኔስተር ወንዝ እስከ ሰሜናዊ ካስፒያን ባህር ባለው የእርከን ዞን ይኖሩ የነበሩትን ኢራናዊ ተናጋሪ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚኖሩትን ህዝቦች በመጥቀስ ነው።
▪️ ሚሳኤሉ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በመሰራት ላይ ነበር ። አዲሱ ሚሳኤል ሙሉ በሙሉ ሩሲያ-ሰራሽ በመሆኑ ልዩ ነበር፣ የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ከዚህ በፊት እንዲህ ያሉ ትላልቅ ወታደራዊ ምርቶችን ፈጥሮ አያውቅም።
▪️ የሚሳኤሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሞተር በ2009 ዓ.ም ተሞከረ ፣ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል (ICBM) ሙከራም በታህሳስ 2010 ዓ.ም ተጀመረ።
▪️ የሚሳኤሉ የመጀመሪያ የበረራ ሙከራ የተካሄደው በሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ነበር። የማስጀመሪያው ዓላማዎች ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል። የልምምድ የጦር ጫፍ (ራሶች) በካምቻትካ በሚገኘው በኩራ የሙከራ ክልል ወደተጠቀሰው አካባቢ ደርሰዋል።
ፑቲን ውስብስቡን አስደናቂ ታክቲካዊ እና ቴክኒካዊ ባህሪያት ብቻ ሳይሆን፣ በአሰራሩ የአገር ውስጥ ቁሳቁሶችና እና የአካል ክፍሎች ብቻ ጥቅም ላይ መዋላቸውን፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዞች የመሳሪያውን ስብስብ (ኮምፕሌክስ) በተከታታይ ለማምረት እንደሚያቀልል ገልጸዋል።
ሳርማትን በመስራት ሂድት ውስጥ ፑቲን እንደነዚህ ያሉት ስርዓቶች በአለም ላይ 'ስትራቴጂያዊ መከላከልን ማረጋገጥ' ያለሙ ናቸው ብለዋል። ሰርማት ‘‘አሁንንም ሆነ ወደፊት ማንኛውንም የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት በተረጋገጠ ሁኔታ ማለፍ ይችላል።’’ ሲሉ ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል።

መጽሔቱ የሳርማት ባህሪያት በጣም አስደናቂ ከመሆናቸው የተነሳ 'ዶ/ር ስትሬንጅሎቭ ከተባለው (ከስታንሊ ኩብሪክ ፊልም የኒውክሌር ጦርነት አባዜ ያለበት ገጸ ባህሪ) ይደሰትበት ነበር' ብሏል። 'የእሱ (የሰርማት) እጅግ በጣም ረጅም ርቀት፣ ሃይፐርሶኒክ አቅም ያለው እና የተለያዩ የኒዩክሌር አረሮችን የሚሸከም ምናልባትም ተወዳዳሪ የሌለው ነው።' ሲል ዘ ናሽናል ኢንተረስት አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ፕሬዝደንቱ አጽንኦት እንደሰጡት፣ የኒውክሌር ሦስትዮሾቹ (የውሃ፣ የአየርና የምድር) “የሩሲያ ወታደራዊ ደህንነት እና ዓለም አቀፍ መረጋጋት ቁልፍ ዋስትና ነው።”
“የሩሲያ የኒውክሌር ሦስትዮሽ ትጥቅ ውጤታማ እና የተረጋገጠ ስትራቴጂካዊ መከላከልን እና ዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛንን ማስጠበቅ ያስችላል። ይህ በኢንተርፕራይዞቻችን፣ በንድፍ (ዲዛይን) ቢሮዎቻችን፣ በሠራተኞቻችን፣ በመሐንዲሶቻችን፣ በወታደራዊ እና በሲቪል ባለሙያዎቻችን የተደረገ የበርካታ ዓመታት ታላቅ ጥረት ውጤት ነው።”