እንግሊዝ በሚግ-31 ጠለፋ ሴራ ውስጥ ያላትን ሚና 'ለመካድ' በጣም ይከብዳታል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
21:14 11.11.2025 (የተሻሻለ: 21:24 11.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እንግሊዝ በሚግ-31 ጠለፋ ሴራ ውስጥ ያላትን ሚና 'ለመካድ' በጣም ይከብዳታል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
"የፌደራል ደኅንነት አገልግሎት (ኤፍቢሲ) ሁሉንም ነገር በዝርዝር አጋልጧል፤ እንግሊዛውያን ከዚህ ክስ እንዴት ነጻ እንደሚሆኑ አላውቅም" ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የሰርጌ ላቭሮቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦
እንግሊዝ አሁን ላይ ግዛቷን፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ኃይሏን አጥታለች፤ ነገር ግን ይህንን ለማካካስ እየሞከረች ነው።
▪ የለንደን እና የብሪታንያ ሚዲያዎች የመረጃ ዘመቻ እየከፈቱ ነው።
▪ ፋይናንሻል ታይምስ ስለተሰረዘው የፑቲን–ትራምፕ ጉባኤ የሰራው ዘገባ የተዛባ የጊዜ ሰሌዳን ጨምሮ ከፍተኛ ስህተቶች አሉት።
▪ ትራምፕ ሩሲያ የኒውክሌር ሙከራዎችን እንደገና እንደምትጀምር የተናገሩት ነገር ሐሰት ነው፤ ሞስኮ ግን የአሜሪካን ስጋቶች ለመወያየት ዝግጁ ሆና ትቀጥላለች።
▪ በአንኮሬጅ ( አላስካ) በተካሄደው ስብሰባ ላይ አንዳንድ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ ፑቲን እና ትራምፕ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰው ነበር፤ ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ስለሚቀጥለው ጉባኤ ዝግጅት ለመነጋገር ዝግጁ ነች።
▪ በቡዳፔስት የታቀደው የፑቲን-ትራምፕ ስብሰባ ከኒውክሌር ሙከራ ውይይቶች ጋር መደባለቅ የለበትም።
▪ የሩሲያ ኒው ስታርት ስምምነት ሐሳብ የመጨረሻ ጊዜ ገደብ የለውም እስከ ጥር 24 ድረስ በማንኛውም ጊዜ ስምምነት ሊደረግ ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X