ኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ
ኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2025
ሰብስክራይብ

ኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት ኤልሳቤጥ ሽልማቱ የተሰጣቸው ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በማሕበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ ኤልሳቤጥ ያገኙት እውቅና በኢትዮጵያ የግብርና ምርምርና ፈጠራን በማላቅ ረገድ ያላቸውን ወሳኝ ሚና እንደሚያጎላ ገልጿል፡፡

“የእሳቸው አመራርና ጽኑ ቁርጠኝነት የኢትዮጵያን የግብርና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዕድገትና ዘላቂነት በከፍተኛ ደረጃ አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ ሰዎችንም ፈለጋቸውን እንዲከተሉ አነሳስቷል።” ብሏል፡፡

ኤልሳቤጥ፣ ሽልማታቸውን ጥቅምት 28 በሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ በተካሄደ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ መቀበላችውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ
ኤልሳቤጥ ባስልዮስ ከ100 የአፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0