ጤና ሚኒስቴር ሦስት ዘመናዊ የጤና አገልግሎት አማራጮችን ይፋ አደረገ
16:24 11.11.2025 (የተሻሻለ: 18:34 11.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጤና ሚኒስቴር ሦስት ዘመናዊ የጤና አገልግሎት አማራጮችን ይፋ አደረገ
ሚኒስቴሩ “ጤንነቴ" የሞባይል መተግበሪያ፣ "ለበጎ” የአምቡላንስ መላኪያ ስርዓት እና 952 ብሔራዊ የጤና ጥሪ ማዕከልን ሥራ አስጀምሯል፡፡
አዲሱ “ጤንነቴ" የሞባይል መተግበሪያ ዜጎች ስለ መድኃኒት አቅርቦት፣ የጤና አገልግሎቶች እና የጤና መረጃ በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል። አገልግሎቱ በአዲስ አበባ በይፋ ሲጀመር በቀጣይ በመላ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ዲጂታል ጤና ሁለንተናዊ የጤና ሽፋንን ለማድረስ እና ጠንካራ የጤና ስርዓትን ለመገንባት ቁልፍ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አፅንዖት ሰጥተዋል ሲል ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ጽፏል።
የጤና መረጃ ለሁሉም ሰው በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የተነደፉ መሆናቸውን በዲጂታል ጤና ጉባኤ ላይ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia