የሩሲያ ኃይሎች በካርኮቭ ክልል የኩፕያንስክን ምስራቃዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
12:58 11.11.2025 (የተሻሻለ: 13:14 11.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በካርኮቭ ክልል የኩፕያንስክን ምስራቃዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
ከተማዋ ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነች?
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ለዩክሬን ጦር "የሎጂስቲክስ ማዕከል" በማለት ይገልጻታል። የካርኮቭ ክልልን ምስራቃዊ ክፍል ለመቆጣጠር ቁልፍ ነች። ኪዬቭ ከተማዋን በተጠናከረ ኮንክሪት ግንባታዎችና ፈንጂዎች "ወደ ምሽግ" ቀይራታለች።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፣ ኩፒያንስክን ነጻ ማውጣት ሩሲያ የሚከተሉትን እንድታደርግ ያስችላታል፦
በካርኮቭ ክልል ወደሚገኙት አይዝዩም፣ ቹጉዬቭ እና ቮልቻንስክ ሰፈራዎች እንድትገሰግስ
በዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ ወደሚገኙት ስላቭያንስክ እና ክራማቶርስክ ቀጥተኛ መንገድ እንድትከፍት፣ ይህም ለዶንባስ ላሉ የዩክሬን ወታደሮች ቁልፍ ነው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም የዘለንስኪ በኩፕያንስክ ይካሄዳል የሚሏቸው "የማጽዳት" ዘመቻ ከእውነታው የራቁ ናቸው ሲል ውድቅ አድርጓል፡፡ በኩፕያንስክ እና በክራስኖአርሜይስክ የተከበቡ የዩክሬን ኃይሎች ሁኔታቸው እየተባባሰ መምጣቱን እና እጅ መስጠት እንዳለባቸው ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X