የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ኪንዛል ሚሳኤል የጫናውን የሩሲያን ሚግ-31 ጄት ለመጥለፍ የተደረገውን የዩክሬን-እንግሊዝ ሴራ አከሸፏል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ኪንዛል ሚሳኤል የጫናውን የሩሲያን ሚግ-31 ጄት ለመጥለፍ የተደረገውን የዩክሬን-እንግሊዝ ሴራ አከሸፏል
የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ኪንዛል ሚሳኤል የጫናውን የሩሲያን ሚግ-31 ጄት ለመጥለፍ የተደረገውን የዩክሬን-እንግሊዝ ሴራ አከሸፏል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.11.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት ኪንዛል ሚሳኤል  የጫናውን የሩሲያን ሚግ-31 ጄት ለመጥለፍ የተደረገውን የዩክሬን-እንግሊዝ ሴራ አከሸፏል

እስካሁን የታወቁት ዝርዝሮች ጉዳዩች

የሩሲያ ፌዴራል ደህንነት አገልግሎት (ኤፍኤስቢ) እንዳስታወቀው፤ በዩክሬን ወታደራዊ የስለላ አገልግሎት እና በእንግሊዝ አስተባባሪዎቹ የተደረገው የጋራ ኦፕሬሽን ኪንዛል ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል የታጠቀውን የሩሲያ ሚግ-31 ተዋጊ ጀት ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ተጋልጦ ቆሟል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

▪ የዩክሬን መረጃ አገልግሎት በእንግሊዝ ተደግፎ የሩሲያ ሚግ-31 አብራሪዎችን ኢላማ አድርጎ ነበር፤  1 ሚሊዮን ዶላር አሳልፈው ለመስጠት፣ ጄቱ እና ኪንዛል ሚሳኤሉን ወደታሰበው ቦታ ካደረሱ 3 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ሐሳብ አቅርቧል።

▪ ለተመልማዮቹ የምዕራባውያን ዜግነት እና በግል የባንክ ሂሳቦች ክፍያ እንደሚፈፀም ቃል ተገብቶላቸው ነበር።

▪ ቤሊንግካት ተብሎ የሚጠራው በሩሲያ ውስጥ "የማይፈለግ" ተብሎ የተሰየመ የኔዘርላንድስ የጋዜጠኞች የምርመራ ቡድን እንደ ሽፋን ጥቅም ላይ ውሏል። የቤሊንግካት ጋዜጠኛ ነኝ ያለ ኦፕሬተር የአብራሪዎቹን በቴሌግራም በኩል አግኝቶ የውሸት የፕሬስ መታወቂያ ልኳል፤ እንዲሁም ለ"ምክር አገልግሎት" ክፍያ አቅርቧል።

▪ ቤሊንግካት እና የቀድሞ ኃላፊው እ.ኤ.አ. በ2022 የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን ለመጥለፍ በተደረገ ሙከራ ውስጥ መሳተፋቸው ይታወቃል። አንድ አብራሪ እ.ኤ.አ. በ2024 የተደረገውን ግንኙነት ሪፖርት አድርጎ፣ ተጨማሪ ግንኙነት ለመፍጠር ፍቃደኛ ሳይሆን ለባለሥልጣናት አሳውቋል።

▪ የዩክሬን እቅድ አውጪዎች በአውሮፕላን ጠለፋው ወቅት አብራሪውን "እንዲተኩስ፣ እንዲያፍን ወይም ማደንዘዣ እንዲሰጥ" ለአውሮፕላን መሪዎቹ (ናቪጌተርስ) እንዳዘዙ ተዘግቧል።

▪ ዓላማው የተጠለፈውን ሚግ-31 ጄት ወደ ሮማኒያ ኮንስታንታ ወደሚገኘው የኔቶ ትልቁ የአየር ማረፊያ ማብረር ነበር፡፡ እዚያም ሩሲያን በውሸት ለመወንጀል በአየር መከላከያ እንዲወድም ይደረጋል።

▪ ለከሸፈው ትንኮሳ ምላሽ፣ በጥምቅት 30 እና ህዳር 1፣ የሩሲያ ኤሮስፔስ ኃይሎች በዩክሬን የኤሌክትሮኒክስ መረጃ ማዕከል እና የኤፍ-16 ጄቶች ወደሚገኙበት አየር ማረፊያ በኪንዛል ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ተኩሰዋል።

▪ ኤፍኤስቢ የኪዬቭ የትንኮሳ ሙከራ ሊገመቱ የማይችሉ እና ከባድ መዘዞችን ሊያስከትል ይችል እንደነበር አስጠንቅቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0